2012-03-05 13:14:24

ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ 50ኛው ዓመት በኋላ፦ የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበራት እና አስፍሆተ ወንጌል


እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 23 ቀን እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. በኢጣሊያ አሲዚ ከተማ ዓለም አቀፍ የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበራት ጉባኤ እንደሚካሄድ ሲገለጥ፣ የዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ RealAudioMP3 ዋና ምክር ቤት አባላት በእቅድ ተይዞ ያለው ጉባኤ ለማዘጋጀት የቅድመ ዝግጅቱ ሂደቱ ለመገንዘብ እና እፍጻሜ ለማድረስ ባለፈው ሳምነት እዚህ ሮማ ቆይታ ማድረጉ የድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
አለ መግባባት በተከናነበው ታሪክ አማካኝነት የእግዚአብሔር ቃል ማዳመጥ፣ የሐዋርያዊ አገልግሎት ሕይወት ገዛ እራስ ስለ መስጠት ይናገራል። በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ የሚካሄድ መሆኑ ከወዲሁ በጅዜፐ ላዝዛቲ ለተመሠረተው የንጉሠ ክርስቶስ የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበር ሊቀ መንበር ጆርጆ ማዞላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ፈር ያስያዘው በሰው ልጅ ሕይወት ተጨባጭ እንዲሆን ያበቃው የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበሮች ጉዳይ በርግጥ የነዚህ ማኅበሮች ተመክሮ እንደሚያመለክተው ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር በማድረግ የሚለዩ በዓለም የሚኖሩት ተመክሮ ነው። ለዚህ ሕይወት የተጥሩት ከሙያቸው ከእለታዊ ኑሮአቸው ሳይለዩ ነገር ግን ለእግዚአብሔር የተሰጡ ናቸው። ስለዚህ በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ መስካርያን ናቸው ካሉ በኋላ ይህ በአሲዚ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝክረ 50ኛው ዓመት ምክንያት የጉባኤው ሰነዶች መሠረት፣ መሠረታዊ መለያቸው የሆነው ጥሪ በዚህ በምንኖርበት ዘመን ሥር በጥልቀት በማጤን ለምንኖርበት ዓለም ተጨባጭ መልስ ለመስጠት ሁሉም በሚሰጠው እና በተሰማራበት የሙያ ዘርፍ በፖለቲካው በማህበራዊው እና በኤኮኖሚ ዓለም ይሁን በሚሰጠው አገልግሎት ለእግዚአብሔር የተሰዋው ሕይወቱን በመኖር ለዓለም ለቤተ ክርስትያን የሚሰጠው አገልግሎት የሚያብራራ ጉባኤ ይሆናል ብለዋል።
የእዚአብሔር ቃል ዘወትር አንድ ነው፣ ሆኖም ከእለታዊው ሕይወት ጋር ተያይዞ ሲነበብ አዲስ ይሆናል፣ ትላትና የተነበበ ቢሆንም ከእለታዊ ሕይወት ጋር የተቆራኘ ቃል በመሆኑ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተረጋገጠው ኅያውነት ቀጣይ ሆኖ ይኖራል። ስለዚህ ከተባለው ቃል መጀመር ሳይሆን ከእለታዊ ሕይወት ጋር በማቆራኘት የተባለው ቃል አዲስነቱን መመስከር የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበራት ዓላማ ነው። የእግዚአብሔር ቃለ ሕይወት በዕለታዊ ሕይወት በመኖር በተሰማራህበት ዘርፍ በቃል እና በሕይወት መመስከር ወሳኝ ነው። ይኽ ምስክርነት የምንኖርበት ዓለም የሚጠይቀው አንገብጋቢ ዓላማ ነው ካሉ በኋላ፣ በቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት ሥር የሚመራ በቤተ ክርስትያን ውስጥ የሚኖር ከቤተ ክርስትያን ጋር በመሆን በተሰማራበት ሙያ ቃለ እግዚብሔር የሚኖር እና የሚበሥር ተልእኮ የሚኖርበት ጥሪ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.