2012-06-18 19:06:41

የእግዚአብሔር ፍቅር ትንሹን ነገር ወደ ታላቅ ነገር ይለውጣል፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመመርኰዝ ባቀረቡት አስተምህሮ በዕለቱ ቃለ ወንጌል ተመርኵዘው “የእግዚአብሔር ፍቅር ትንሹን ነገር ወደ ታላቅ ነገር ይለውጣል” ሲሉ ድካማነታችን እግምት ውስጥ ሳናስገባ የሚገባንን በቍርጠኝነት ያደረግን እንደሆነ ቀሪውን እግዚአብሔር እንደሚፈጽመው አረጋግጠዋል፣ የዕለቱ ቃለ ወንጌል ከወንጌል ማርቆስ ምዕራፍ 4፤26 የተወሰደ “በምድር ዘርን እንደሚዘራ ሰው የእግዚአብሔር መንግሥት እንደዚህ ናት ሌሊትና ቀን ይተኛልም ይነሣልም፥ እርሱም እንዴት እንደሚሆን ሳያውቅ ዘሩ ይበቅላል ያድግማል። ምድሪቱም አውቃ በመጀመሪያ ቡቃያ ኋላም ዛላ ኋላም በዛላው ፍጹም ሰብል ታፈራለች። ፍሬ ግን ሲበስል መከር ደርሶአልና ወዲያው ማጭድ ይልካል። እርሱም አለ። የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እናስመስላታለን? ወይስ በምን ምሳሌ እንመስላታለን? እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት ናት፥ እርስዋም በምድር በተዘራች ጊዜ በምድር ካለ ዘር ሁሉ ታንሳለች፤ በተዘራችም ጊዜ ትወጣለች ከአትክልትም ሁሉ የምትበልጥ ትሆናለች፥ የሰማይ ወፎችም በጥላዋ ሊሰፍሩ እስኪችሉ ታላላቅ ቅርንጫፎች ታደርጋለች፣” የሚል ነበር፣
ቅዱስነታቸው ይህንን ተመርኵዘው፤ እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት ዘር ትርጉም የሌለው ታናሽ ነገርን የሚለውጥ የእግዚአብሔር ፍቅር መሆኑን በማስመር የእግዚአብሔር ፍቅር ታላቅነት በቃለ እግዚአብሔር መሆኑን አገንዝበዋል፣ ደካማነት የዘር ኃይል መሆኑ ሞቶ ተቀብሮ ለመብቀል መቻሉ ደግሞ የዙሩ ችሎታ መሆኑንንም አብራርተዋል፣ ይህ ምሳሌ የእግዚአብሔር መንግሥት ምሳሌ መሆኑን ለማስረዳት ሲያስተምሩ “በሰው ልጅ አመለካከት እጅግ ታናሽ የሆነችው በእግዚአብሔር ፍቅር ኃይል እንጂ በዓለም አመለካከት ብቃት በሌለው በኃይሉ በማይተማመን የተቋቋመችው ታናሿ የሰናፍጭ ዘር፤ በምንመለከትበት ጊዜ የክርስቶስ ኃይል በእንዚህ ትርጉም አልባ ነገሮች ድንቅ ነገሮች ሲፈጽምና ነገሮችን ሲለውጥ እናያለን፣ የእግዚአብሔር መንግሥት የእኛ መታባበር ቢያስፈልገውም ቅሉ በመሠረቱ የጌታ ስጦታ ነው፣ በዚህም በዓለም በሚከሰቱ ትላልቅ ችግሮች የእኛው ትንሽ ኃይል በእግዚአብሔር የሰጠመች እንደሆነ ምንም ዓይነት ዕንቅፋት ቢገጥማትም አትሸነፈም ምክንያቱም የጌታ ድል እርግጠኛ ስለሆነ ነው፣ ይህም ዘሩን እንዲበቅልና አድጎ መልካም ፍሬ እንዲሰጥ የሚያደርግ የእግዚአብሔር ፍቅር ተአምር ስለሆነ ነው፣ ያለነው ጊዜ የዘር ጊዜ ነው፤ የዘሩ መብቀልና ለፍሬ መድረስ የጌታ ፈንታ ነው፣
የመንግሥቱ ጌታ የሆነው እርሱ ነው፣ ይህንን ነገር የሚያስተንትን እና በዚሁ መለኮታዊ ተግባር የሚደሰት እንዲሁም በትዕግሥት ፍሬውን የሚጠባበቅ ትሑት ተባባሪ የሆነው የሰው ልጅ ነው፣ የመጨረሻው የመኸር ጊዜ የሚያስተምረን ነገር ካለ በዓለም መጨርሻ ላይ እርሱ መንግሥቱ በሙላት እውን ካደረገ በኋላ ስለሚያደርገው ፍርድ ያሳስበናል፣ ሆኖም ግን ትንሹ የሰናፍጭ ዘር ቢደቅም የሕይወት ሙላት እንዳለውና በሕይወት ሲፈካ መሬቱን በርግዶ ሊበቅል እንደሚችላና ከአትክልቶች ሁሉ በላይ ትልቅ እስኪሆን ለማደግና የጸሓይ ብርሃን ሊያገኝ እንዲሚችል ማወቅ ያስፈልጋል፣ ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስትያን ማድረግ የሚችለውን ሁሉ መፈጸም እንዳለበት ያውቃል ሆኖም ግን የመጨረሻው ውጤት ከእግዚአብሔር እንደሚወሰን ያውቃል፣ ይህ ዕውቀት በየዕለቱ በሚያካሄደው ትግል በተለይ ደግሞ አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ይደግፈዋል፣ ይህንን በተመለከተ ቅዱስ ኢግናጽዮስ ዘሎዮላ “ሁሉ ነገር በእግዚአብሔር እንደሚወሰን ብታውቅም ቅሉ ሁሉ ባንተ እንደሚወሰን አድርገህ ስራ” የሚለውን ማስታወስ ያስፈልጋል ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.