2012-10-09 10:13:47

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በሎረቶ ሐዋርያዊ ዑደት


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትናው ዕለት በሎረቶ ባደረጉት ሐዋርያዊ ዑደት እላይ እንደተጠቀሰው በቦታው ተገኝተው የተቀበልዋቸው ምእመናን ከ10 ሺ በላይ እንደሚሆኑ እንዲሁም መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ጊዜም በተለያዩ የሎረቶ አደባባዮችና ጐዳናዎች ከ50 ሺ ሕዝብ በላይ በመገናኛ ብዙሓን እንደተሳተፉ ከቦታው የመጣ ዜና አመልክተዋል፣ ከከተማው ከንቲባ ፓውሎ ኒኮለቲ ጀምሮ የመንግሥት ባለሥልጣናትም ይሁኑ የቤተ ክርስትያን ባለሥልጣናት የተለያዩ ዲስኩሮች አቅረበዋል፣
የቫቲካን ረድዮ ጋዜጠኛ በበዓሉ ፍጻሜ ለከተማው ከንቲባ አቶ ኒኮለቲ በጉብኝቱ የረኩ እንደሆነ ጠይቆዋቸው ሲመልሱ፣ በቅዱስ አባታችን ጉብኝት እጅግ ረክቻለሁ እንዲሁም የሎረቶ ከትማ ባሳየችው ዝግጅትና ቅዱስነታቸው ባቀረብዋቸው ሥር ዓተ አምልኮና ልመናዎች የማኅበረሰቡ ሱታፌ እጅግ የሚያረካ ነበር፣ ከዚህም ባሻገር የቅዱስነታቸው ጉብኝት ሎረቶ እንደ መካነ ንግደት ምን ያህል አስፈላጊነት እንዳላትም አጉልቶ አሳይቶዋል ሲሉ ገልጠዋል፣
በዚሁ ጉብኝት እርካታቸውን ከገለጡ ደግሞ ምክትል ጸሐፊ ካትሪካላ ሆኖ በተለይ ቅዱስነታቸው ያለነውን ሁኔታ አውስተው በተለይ ስላለው ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስና በቤተሰብና በወጣቶች ስለሚያስከትለው ችግር ሲግልጡ ሰብአዊ ዕሴቶችን በማክበርና በእምነት መፍትሔ ሊገኝ እንደሚችል የሰጡት አስተምህሮ ለጊዜው የሚበጅ ነው፣ መራሔ መንግሥት ሞንቲም ይህንን ነው የሚሉት፣ ብዙ መሥዋዕት እየከፈልን ነው፣ ተስፋችን እንደገና ለመነሣት ነው፣ ቅዱስነታቸው እንዳሉትም ተስፋዎቻችንና የመላው ዓለም ተስፋዎችን በሎረቶ ድንግል ማርያም እናማጥናለን ሲሉ የተሰማቸውን እርካታና ደስታ ገልጠዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.