2012-10-17 14:39:20

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ አዲስ ክርስትያናዊ ጸደይ እየታየ ነው


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ክርስትና የኤውሮጳ ባህልና የክፍለ ዓለሟ መጻኢ መካከል ያለው ግኑኝነት ላይ ያነጣጠረ “የኤውሮጳ ደወል” በሚል ርእስ ሥር በአባ ጀርማኖ ማሪያኒ የተወጠነ የግረጎሪያና ማኅበር ከሚገኙባቸው ከተለያዩ ተቋሞች ድጋፍ በማግኘት በቫቲካን የቴሌቪዥን ማእከል ገቢራዊ ሆኖ ራይ በመባል በሚጠራው የኢጣሊያ የድምጸ ርእይ ጣቢያ አማካኝነት በቪዲዮ ተቀርጾ የሚሰራጭና በዚሁ የቴሊቪዥን ጣቢያ ለትርኢት የሚቀርበው ሰነዳዊ ፊልም በአገረ ቫቲካን በመካሄድ ላይ ባለው የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ ተሳትፋፊዎች ውስጥ የታደሙበት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተገኙበት የፊልሙ ጽማሬ ሃሳብ ለትርኢት መቅረቡ ሲገለጥ፣ ይህ ሰነዳዊ ፊልም የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፣ የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስታይን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ አንደኛ፣ የሞስኮና የመላ ሩሲያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ RealAudioMP3 ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል፣ የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሮዋን ዊሊያምስ፣ የቀድሞ የጀርመን ፈደራላዊ ወንጌላውያን አቢያተ ክርስትያን ሊቀ መንበር ሁበር እንዲሁም የኤውሮጳ አንዳንድ አበይት የፖለቲካና የባህል አካላት የሰጡት የቃለ መጠይቅ መልስ ያካተተ ሆኖ፣ የፊልሙ ውሁድ ጥዑም ሙዚቃ ደራሲ ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው ውስጥ አንዱ የኤስቶኒያ ተወላጅ የሙዚቃ ሊቅ መምህር አርቮ ፓርት መሆናቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ በፊልሙ ከተቀረጸው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ የሰጡት መልስ፦ ቅዱስነታቸው እስካሁን ድረስ በደረሱዋቸው አዋዲ መልእክቶቻቸው አማካኝነት አንድ በእግዚአብሔር ፍቅር የተኖረበት፣ የእምነት ተመክሮ አማካኝነት ሰፊ ተገናኝነት ያለው፣ አንቀሳቃሽ በሆነው በእውነት የሚቀበለውና የሚለግሰው ፍቅር በማኅበራዊ ኑሮ ኃላፊነት መሆኑ የሚገልጥ አዲስና ብርቱ ስነ ሰብእ ያቀርባሉ፣ በዚህ መሠረትም በእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ የተፈጠረው ሰው ከሚያደበዝዙት ከተለያዩ እክሎች በማላቀቅ ዳግም እንዲረጋገጥ ያሳሰቡት፣ አዲስ በወንጌላዊ እሴቶች ላይ የጸና ጥልቅ የኤውሮጳ አናስር የሆነው ሰብአዊነት ለኤውሮጳ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ጭምር አቢይ ተስፋ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው ይኽ ያሉበት ምክንያትም ሲያብራሩ፦ “በውስጣችን ያለው እግዚአብሔር የመሻትና የመፈለጉ በእያንዳንዱ ሰው መንፈስ ዘንድ ያለው ምክንያት ነው። ስለዚህ ይህ ውስጣዊው ግፊት ፈጽሞ ለማጥፋት አይቻልም፣ በርግጥ ለተወሰነ ጊዜ እግዚአብሔርን ረስቶ እርሱን ወደ ጎን በመተው በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተጠምዶ መኖር ይቻል ይሆናል፣ ሆኖም ግን እግዚአብሔር ፈጽሞ አይጠፋም፣ ቅዱስ አጎስጢኖስ እንደሚለውም ሰው እግዚአብሔርን እስከሚያገኝ ድረስ መንፈሰ ጭንቀታም ነው። ይህ ጭንቀት አሁንም አለ፣ ስለዚህ ዛሬም ቢሆን የሰው ልጅ ዳግም ወደ እግዚአብሔር የሚል ነው። በሁለተኛ ደረጃም...ካላቸው ልምድ አንጻር…የጌታችን ኢየሱስ ክትስቶስ ወንጌልና በክርስቶስ ላይ ያለን እምነት እውነት ነው። እውነትም ፈጽማ አታረጅም፣ ለተወሰነ ጊዜ በሌሎች ማለት ከታሪክ እንምደምንረዳውም በተለያዩ ጨርሰው ሊጠፉና ሊሞቱ ያማይችሉ ዘለዓለማዊ ተመስለው በሚሰበኩትና በተሰበኩት ርእዮተ ዓለም በመተካትም የሚዘነጋ እውነት ሊሆን ይችል ይሆናል፣ ሆኖም ግን ገዛ እራስ እውነትን ለማጥፋት ግን አይቻልም፣ ተስፋ የተጣለባቸው ርእዮተ ዓለሞች እውነት ሊሆኑ ስለማይችሉና ባለ መሆናቸውም አንድ በአንድ ሲያከትሙ አይተናል፣ የሰው ልጅ ለወሰነ አልቦነት ያቀና ፍጡር ነው። ስለዚህ በአዲስ ትውልድ ዘንድም የተጨነቀች መንፈስ ዳግም በመነቃቃት ወደ እውነተኛው የክርስትናው ውበት እንዲያቀኑ እያደረገ ነው። ለገበያ በማይወርደው ልመሳሰል በማለት ገዛ እራሱን በማያዋርድ ክርስትና ይማረካሉ፣ ስለዚህ ክርስትና እውነት ነው እውነትም ዘወትር መጻኢነት አለው” ብለዋል።
ኤውሮጳ በጠቅላላ ሰብአዊ ባህል ዘንድ ተጽእኖ እንዳለውና ስለዚህ ስለ ገዛ እራስ መጻኢ ብቻ ሳይሆን ለተቀረው ዓለም መጻኢነትም ኃላፊነት አለው፣ ኤውሮጳ ለክርስቶስ ታማኝ እንግዳ ተቀባይ አስተናጋጅ ባህርይዋ ለሚገልጣት ከክርስትናው እምነት ለተወረሰው ባህል በአሁኑ ወቅት ለምትኖረው አቢይ ተጋርጦ ኅብረ ባህልና ኅብረ ሃይማኖት በትክክል ለመኖርና ለመወያየት መሠረት ነው ያሉበትን ምክንያትም ሲያብራሩ፦ “ኤውሮጳ በአሁኑ ወቅትም በዓለም ደረጃ ኤኮኖሚያዊ ባህላዊና እውቀታዊ ተጽእኖ አላት፣ ከዚህ አንጻር በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለባት ኃላፊነት ምንኛ አቢይ መሆኑ ለመገመቱ አያዳግትም፣ ስለዚህ ይኽ ሂደት ኤውሮጳ ካላት ኃላፊነተ አንጻር ከሌሎች ጋር ለመወያየትና ለመወሰን የገዛ እራሷ ትክክለኛው መለያዋ መትክክል ማወቅ ይኖርባታል። በአሁኑ ወቅት ያለው አቢይ ችግር የአገሮች ልዩነትና ብዙኅነት ሳይሆን መከፋፈል ነው። ስለዚህ አገሮች ያላቸው ባህላዊ ልዩነት እንደ ሃብት በመኖር የተለያየው ባህል ውሁድ ጥዑም ሙዚቃ የሚያቀነቅን የሙዚቃ ድርሰት እንደሆነ አድርጎ መገንዘብ አስፈላጊ ነው።
በአሁኑ ወቅት በኤውሮጳ ሁለት መንፈስ ነው ያለው፣ አንዱ የማይዳሰስና የማይጨበጥ አመክንዮ ይኽ ደግሞ ጸረ ታሪክ ማለትም የገዛ እራስ ባህል በሌላው ላይ ተጽእኖ በማድረግ መኖር የሚልና የሌላው ባህልና ትውፊት ማግለል፣ በማስወገድ የገዛ እራስ አመለካከት ማንሰራፋት ለዚህም አብነት በስትራስበርግ ፍርድ ቤት የስቁል እየሱስ ምልክት ከማኅበራዊ ስፍራ ሁሉ ማንሳት በማለት ተሰጥቶ የነበረው የመጀመሪያ የፍርድ ቤት ችሎት ውሳኔ ለመጥቀስ ይቻላል፣ ስለዚህ ገዛ እራስ ነጻ ለማውጣት በማለት ከታሪክ ጭምር ነጻ ለማድረግ የሚሞክር ነው። ሁለተኛው ደግሞ ንጹሕ አመክንዮ ነው፣ ይኽ ማለት ደግሞ አስተያየትና እንዲሁም በሳል ግምገማ ለመስጠት የሚያግዝ የአመክንዮ የላቀው ደረጃና ነጻነት የሆነው ክርስትና ለማለት ይቻላል። ይኽ ደግሞ አመዛዛኝነት አበይት እሴቶችን ያመነጨም ነው። በነዚህ እሴቶች መሠረት ያለው አንድነት ማጉላት ማለት ከሌሎች ባህሎችና ሃይማኖቶች ጋር ለመወያየት ለተገባ ትውውቅ ዝግጁ መሆን ማለት ነው። ሰብአዊነት የሚያድገው ሰው የእግዚአብሔር አምሳያና አርአያ መሆኑ የሚያረጋግጠው ሥነ ሰብእ በማክበር ብቻ ነው” በማለት የሰጡን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.