2012-10-17 18:14:41

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች
የዛሬው አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቤተ ክርስትያናችን የቫቲካን ሁለተኛ ጉባኤ መጀመር 50ኛ ዓመትን በማስታወስ የምታካሄደው የእምነት ዓመትን የሚሸኝ በተከታታይ የሚቀርብ አዲስ የትምህርተ ክርስቶስ ዝግጅት ለማቅረብ እወዳለሁ፣ የእምነት ዓመት ያለንን በኢየሱስ ክርስቶስ የማመን ስጦታ በአዲስ መንፈስ ልናሳድስ ጥሪ ያቀርብልናል፣ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ኢየሱስ የሰው ልጅ ሕይወት የመጨርሻ ትርጉም ያሳየናል፣ እምነት ሕይወታችንን ይለውጣል፣ ይህንን የሚያደርገው ፈጣርያችን እግዚአብሔርን ልናወቅውና ልናፈቅረው በማስቻል ነው፣ ነጻ በሆነ ምርጫችን በፈቃዱ እንድንኖርና በእውነት ሰብአዊና ወንድማማችነት ያለው ኅብረተሰብ ለመንገንባት እንድንተባበር ነው፣ ስለዚህ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህⶂአችን የእምነት መሠረታዊ ሓቆች ሓዋርያት በደረሱት ጸሎተ ሃይማኖት እንደተገለጸው ሊመለከት ነው፣ የእምነት ዓመት ም እመናን የክርስቶስን ምስጢር በሙላት እንዲያውቁና አካሉ በሆነች ቤተ ክርስትያን ሕይወት በጥልቀት እንዲሳተፉ ይርዳቸው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.