2012-11-23 14:11:55

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለወህኒ ቤቶች መስተዳዳር አባላት መሪ ቃል ለገሱ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና በአገረ ቫቲካን የ17ኛው የኤውሮጳ የወህኒ ቤቶች መስተዳድር ምክር ቤት አባላት ጉባኤ ተሳታፊዎችን ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው ሲገለጥ፣ የተካሄደው ግኑኝነት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ካጥናቀሩት ዘገባ ለመረዳት አንደተቻለውም፦ “ወህኒ ቤቶች በእስረኛው ላይ በተበየነው የእስራት ገደብ ላይ ማተኮር ብቻ ሳይሆን፣ የዳግመ ሕንጸትና የማረሚያ አገልግሎት መስጫ ናቸው የሚለው መሠረታዊ መለያቸው እና ዓላማቸውንም ዳግም በመኖር፣ እስረኛው ከወህኒ ቤት ነጻ መለቀቅ በኋላ ከኅብረተሰብ ጋር በሰላም ተቀላቅሎ ለመኖር እንዲችል የሚታነጽበት ሥፍራ መሆን ይገባዋል” እንዳሉ አስታውቀዋል።
በዚህ በተካሄደው ግኑኝነት የኢጣሊያ የሕግና ፍትህ ጉዳይ ሚኒ. ፓውላ ሰቨሪኖ መሳተፋቻቸውም ጂሶቲ ገልጠው፣ ሚኒስትሯ ባሰሙት ቃል፦ የወህኒ ቤቶች ኅዳሴ አስፈላጊ መሆኑና ኅዳሴውም በወህኒ ቤት የማቆየቱ እርምጃ በሌላ ተስተካካይ አማራጭ እቅድ ማሟላት የሚለውን መርህ የሚከተል ነው” እንዳሉ ገልጠዋል።
ፍትሐ ብሔርና ፍትሐ ኵነኔ የወንጀል መቅጫ ሥርዓት ብቻ አድርጎ ከመመልከቱ ይልቅ፣ የሰው ልጅ ክብር ዋስትና ላይ ያነጣጠረ መሆኑ እንደሚገባው ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባሰሙት መሪ ቃል በማሳሰብ፣ ስለዚህ ለዳግመ ሕንጸትና እሥረኛ ዳግም ከህብረተሰብ ጋር ተቀላቅሎ ለመኖር የሚያግዘው ሕንጸት የሚቀስምበት ልዩ ሥፍራ መሆኑ አለበት ብለዋል። “ወህኒ ቤቶች ወንጀለኛው የሚቆይባቸው ማእከል ናቸው ስለዚህ የቆይታው ገደብ የዳግመ ሕንጸትና ኅብረተሰብ በተለያየ ወንጀል የተገለለው አባል ዳግም በእቅፉ ለመቀበል ላለው ሰብአዊ ፍላጎት ማስተግበሪያና እስረኛው ዳግም ታንጾ ለማህበራዊ ጥቅም መረጋገጥ ንቁ ተወናያን እንጂ ለኅብረተሰብ አደጋ ሆኖ የእንዲታይ ጣት የሚቀሰርበት ሥፍራ መሆን የለባቸውም” ካሉ በኋላ አያይዘውም፣ “ወህኒ ቤቶች የሰብአዊ ክብር ጋር የተስተካከለ ቅርጽ ሊኖራቸው ይገባል” እንዳሉ ጂሶቶ አስታወቁ።
“ፍትሐ ብሔርና ፍትሐ ኵነኔ ወንጀለኛነት ማረጋገጫና እርምጃ ማስፈጸሚያ አድርጎ መመልከት ሳይሆን ወንጀለኛ ማረም እና ዳግሞ ማነጽ ዓላማ ላይ ያነጣጠረ መሆን አለበት”፣ ካሉ በኋላ በወህኒ ቤት የሚያገለግሉት ሠራተኞችና የወህኒ ቤት መስተዳድር አባላት የወህኒ ቤቶች ጸጥታ አስከባሪ አባላት ያለባቸው ኃላፊት ዓቢይ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ገልጠው ይኸንን አገልግሎት በተረጋጋና በቅንነት የሚፈጽሙ ሁሉን አመስገነዋል።
“ቅዱስነታቸው በወህኒ ቤት የሚገኙት የውጭ አገር ስደተኞችን በማስታወስ፣ ስደተኛው በተለያየ መልኩ ለተለያየ አደጋ የተጋለጠ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኝ መሆኑ በማስታወስ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠውና ተገቢ ሕንጸት እንደሚያሻው መዘንጋት የለበትም፣ ስለዚህ በወህኒ ቤት የሚገኘው ስደተኛ እስረኛ ከሚያጋጥመው ተገሎና ተነጥሎ ከመኖር ሁኔታ እንዲላቀቅ የተሟላ ድጋፍ እንዲቀርብለት አደራ” ካሉ በኋላ በወህኒ ቤቶች አስፍሆተ ወንጌል ላይ ያተኮረ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በዚህ ዘርፍ አቢይ አስተዋጽዖ ያለው መሆኑና እስረኛው ዳግሞ የመኖር ፍላጎትና የሕይወት ፍቅር ኖሮት የእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ መሆኑ ያለው ውበት ዳግም እንዲገነዘብ የሚያነቃቃ” መሆኑ አብራርተው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.