2013-01-09 15:13:35

የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 ዝክረ 20ኛው ዓመት እየተከበረ ያለው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ርእስ ሥር የቫቲካን ረዲዮ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ዳሪዩስዝ ኮዋልዝይክ የተመራ የሚያቀርበው ተከታታይ የሥርጭት መርሃ ግብር በመቀጠል ትላትና ባቀረቡት በዘጠነኛው የስርጭት መርሃ ግብር፦ “ር.ሊ.ጳ.ና ብፁዓን ጳጳሳት ልዩ የእምነት ቅርስ ተርጓሚዎች ናቸው” በሚል ርእስ ሥር በማተኮር የታቀበው የእምነት ቅርስ የመተርጎሙ ኃላፊነት ለር.ሊ.ጳ.ና ለብፁዓን ጳጳሳት ሥልጣናዊ ኃላፊነት በእማኔ የተሰጠ መሆኑ አስምረውበታል።
የቤተ ክርስቲያን ትውፊት መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ ግልጸት የሚያስተላልፉት ሁለት መንገዶች የአንድ ቋሚ ተጨባጭ ሐሳብ ቅርጽ ሳይሆኑ፣ ለማኅበረ ሰብ ቤተ ክርስቲያን በእማኔ የተሰጠ ዘወትር በተመሳሳይ መልኩም ለሐዋርያት ትምህርት ታማኝ በመሆን የሚታቀብ በግብር የሚፈጸም የእማኔ ኑዛዜ የሚፈጸምበት ነው። ይህ ታማኝነት ካለ ምንም ጥልቅ ግንዛቤ ተመሳሳይ ቀመር ላለ መፈጸም ቀጣይ የሆነ ትርጓሜ ይጠይቃል። ስለዚህ ከጊዜው ቋንቋ ጋር በሚሄድ አነጋገር ያንን የእምነት ሚሥጢር ለመግለጥ መጣጣር ይኖርብናል።
የቅዱስ መጽሓፍና ቅዱስ የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ትርጓሜ የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት ወይንም ተቀባይነቱ አይለውጠውም፣ ባንጻሩ ለተአምኖተ እምነት በማንኛውም ዘመን ትውልድና ባህል ታማኝ የሆነ ሊተው የማይቻል መሠረታዊ አስፈላጊነትነቱ ያጸናል። የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቁ. 85፦ “በጽሑፍም ሆነ በትውፊት ለተወረሰው የእግዚአብሔር ቃል ትክክለኛው ትርጉም የመስጠት ተግባር ለቤተ ክርስቲያን ሕያው የማስተማር ሥልጣን ብቻ አደራ የተሰጠ ኃላፊነት ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ያላት ሥልጣን በተግባር ላይ የሚውለው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው። ይህም ማለት የመተርጎም ኃላፊነት የጴጥሮስ ተከታይ ከሆኑት የሮማ አርእሰተ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ሱታፌ ላላቸው ጳጳሳት በአደራ ተላልፏል ማለት ነው” ሲል ያብራራል። ይኽ ደግሞ በዮሓንስ ወንጌል ምዕ. 16 ቁ. 13፦ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል ምክንያቱም እርሱ የሚናገረው የሰማውን እንጂ የራሱን አይደለም። እርሱ ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ይነግራችኋል” በማለት የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን የተፈጸመው የኢየሱስ ቃል ኪዳን ተጨባጭ ክንዋኔውን ማገልገል ማለት እንደሆነ ያረጋግጠዋል።
የመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ ወይም መርህነት፣ እውነት ልክ በብዙሃኑ የሰብአዊ አስተያየት የሚወሰን እንደሆነ በዴሞክራሲያዊ ስልት የሚከናወን አይደለም፣ በቤተ ክርስቲያን ሙላት ይንቀሳቀሳል፣ እጅግ ወሳኝና አንገብጋቢ በሆነው ወቅት በቤተ ክስቲያን ሥልጣን አማካኝነት ይናገራል፣ ስለዚህ ለገዛ እራስ ደስ እንደሚያሰኝ አድርጎ እምነት ከማቆም መጠንቀቅ ይገባል። ይኽ ደግሞ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ፦ “…እናንተን የሚሰማ እኔን ይሰማል…” (ሉቃ. ምዕ 10.16) በሚሉት ቃላቶቹ አማካኝነት ይገልጥልናል በማለት አባ ኮዋልዝይክ ያቀረቡት አስተምህሮ አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.