2013-01-21 17:54:05

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


ውድ ውንድሞችና እኅቶች፤ የዛሬው ቃለ ወንጌል በቃና ዘገሊላ ስለተደረገው ሠርግና የኢየሱስ የመጀመርያው ተአምር ይናገራል፣ ይህንን ታሪክ የሚነግረው ቅ.ዮሐንስ ወንጌላዊ ሲሆን በፍጻሜው ላይ በመገኘትም የዓይን ምስክር ሆኖ ይተርከዋል፣ ይህ ፍጻሜ ከጌታ ልደት በዓልና የምሥራቅ ጠበብት ጉብኝት እንዲሁም ከጥምቀት በኋላ መቅረቡ በአስተርእዮ የሚታወቅ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥን በሶስት ደረጃ ያቀርብልናል፣ የቃና ዘገሊላ ሠርግ ፍጻሜ የኢየሱስ ተአምራቶች የመጀመርያው ሲሆን በዚህም በሕዝብ መካከል ክብሩን እንደገለጠ እንመለከታልን፣ ተከታዮቹ ይህንን ተአምር ባዩ ግዜ እምነታቸው እንደጠነከረም ተመልክተዋል፣ መለስ ብለን ታሪኩን የተመለከትን እንደሆነ፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ተከታዮቹ በቃና ዘገሊላ ሠርግ ይሄዳሉ፣ በሠርጉ መካከል ወይን ሲጨረስ እመቤታችን ድግንል ማርያም ለልጅዋ ኢየሱስን ወይን የላቸውም ስትል ታሳስበዋለች፣ እርሱ ግን ገና ሰዓቱ እንዳልደረሰ ይነግራታል ሆኖም ግን የእናቱን ልመና እንዲያው ሊያልፈው ስላልፈለገ ስድስት የድንጋይ ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው። አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም። አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ። ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል እስከማለት ያደረገ እጅግ ጥሩ የወይን ጠጅ ሆነ፣ ኢየሱስ በዚሁ ተአምር እርሱ መሲሓዊ ሙሽራ መሆኑንና ከሕዝቡ ጋር አዲስና ዘለዓለማዊ ኪዳን ያቆማል፣ ይህንም ነቢያት “ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል” (ኢሳ 62፤5) በማለት ስለኢየሩሳሌም የተናገሩት እንዲፈጸም ነው፣ የወይን ጠጁም የዚሁ አዲስ ፍቅር ደስታ ምልክት ነው፤ ሆኖም ግን ይህ የወይን ጠጅ ኢየሱስ ከሰው ልጅ ጋር ያለውን ኪዳኑን ለማተም በመጨረሻ በመስቀል ላይ የሚያፈሰው ደሙንም ያመለክታል፣
ይህች የኢየሱስ ሙሽራ ቤተ ክርስትያን ናት፣ እርሱም በጸጋው ቅድስትና ንጽሕት ያደርጋታል፣ ይህች ሙሽራ በሰው ልጆች የቆመች በመሆንዋ መጠን ሁሌ ጽዳት ያስፈልጋታል፣ የዚች ቤተ ክርስትያን ገጽታን ከሚያቆⶥሹ ሓጢአቶች አንዱ በውስጥዋ የሚታዩ መክፈፋሎች ያ ጌታ አደራ ያለውን አንድነትን ሲፈታተን ነው፣ እነኚህ ታሪካዊ መከፋፈሎች ክርስትያኖችን ከፋፍለዋል ገናም እየከፋፈሉ ናቸው፣ ለዚህም ነው በዚሁ ቀናት ከጥር 18 እስከ ጥር 25 ዓመታዊው ስለ ክርስትያን አንድነት በሚደረግ ጸሎት እያሳረግን ያለነው፣ ይህ አጋጣሚ ለክርስትያኖችም ይሁን ለማኅበሮቻቸው እጅግ አስፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም በሁሉም ክርስትያኖች ዘንድ የክርስትያን አንድነት ፍላጎትን እንዲያነሳሳና እያንዳንዳቸው ለፍጹም አንድነት ተግተው እንዲጥሩ መንፈሳዊ ኃላፊነታቸውን የሚወጡበት ጊዜ ነው፣ ለዚሁ እንቅሳቃሴ እንዲረዳ ከአንድ ወር በፊት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተደረገው የመላው ኤውሮጳ ወጣቶችና የኢኩመኒካዊ የተዘ ማኅበር ነጋድያን ጋር ጸሎተ ሌሊት የተሳተፍኩት ሥር ዓት በክርስቶስ አንድ ለመሆን የሚደረገው ጥረት ምንኛ የጸጋ ጊዜ መሆኑን አይቻለሁ፣ የዚሁ ዓመት የክርስትያን አንድነት ጸሎት ሳምንት መሪ ቃል እንደሚለው ሁላችን ጌታ ከእኛ የሚፈልገውን እውን ለማድረግ እስክንችል ተግተን እንድንሠራና እንድጸልይ አበረታታለሁ፣ ይህ የሚክያ ነቢይ ቃል በህንድ አገር ከሚገኙ ማኅበረ ክርስትያን የተመረጠ ሲሆን በክርስትያኖች ሁሉ መካከል ተጨባጭ አንድነት እንዲኖር በርትተን መሥራት እንዳለብንና እንደኢየሱስ ክርስቶስ ውንድሞች በመካከላችን ያለውን መለያየትና ኢፍትሓዊነት ማሸነፍ አለብን፣ እፊታችን ዓርብ በዚሁ የክርስትያን አንድነት ጸሎት ሳምንት ፍጻሜ ላይ በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ከተለያዩ አብያተ ክርስትያናት ተወካዮች ጋር አብረን ጸሎት እናሳርጋለን፣
ውዶቼ ከዚሁ የክርስትያን አንድነት ጸሎት ጋር ሌላ ለመጨመር የምፈልገው ስለ ሰላም ኃይለኛ ጸሎት ማሳረግ አለብን ምክንያቱም በተለያዩ አገሮች ያሉ ግጭቶች እንዲቆሙና ሁሉ ዓመጽ ዛሬውኑ እንዲወገድ እንዲሁም ያሉትን ችግሮች በድርድር ለመፍታት ብርታት እንዲያገኙ መጸለይ የግድ ስለሚያስፈልግ ነው፣ ለዚሁ ሁሉቱ የጸሎት አሳቦቻችን እመቤታችንና የጸጋ አማላጅ የሆነች ድንግል ማርያም እንትረዳን እንማጠን፣
ትናንትና ከመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ በኋላ ቅዱስነታቸው በቅርቡ በጀመሩት የትዊተር መገናኛ ብዙኃን በላቲን ቋንቋ ለመጀመርያ ጊዜ አጭር መል እክት እንደጻፉ ተመለከተ፣ የመል እክቱ ይዘትም ጌታ ለክርስትያን አንድነት ከእኛ የሚጠብቀው ምንድር ነው፧ ለመቋረጥ ጸሎት ማሳረግ ፍትሓዊ መሆን በጎነትን ማፍቀርና ከእርሱ ጋር እንድንጓዝ ነው፣ ይላል







All the contents on this site are copyrighted ©.