2013-05-08 17:23:15

መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ሁላችንን እንደ እውነተኛ አባት እንደሚያፈቅረን ያስተምረናል፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ትምህርታቸውን ለመስማትና ሐዋርያዊ ቡራኬአቸውን ለመቀበል ከሁሉም የዓለም ክፍሎች ለተሰበሰቡ ከአንድ መቶ ሺ በላይ ለሚሆኑ ነጋድያንና ምእመናን ስለመንፈስ ቅድስ ባቀረቡት ትምህርት RealAudioMP3 ጓደኞቻችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ልብ እንድናፈቅር እንደሚያስተምረን ከገለጡ በኋላ “መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ሁላችንን እንደ እውነተኛ አባት እንደሚያፈቅረን ያስተምረናል፣ ሆኖም ግን ይህንን እንዴት ለማረጋገጥ ይቻላል? መንፈስ ቅዱስን ጸጥ ብሎ በማዳመጥ ምክንያቱም እርሱ ብቻ ነው በእግዚአብሔር እንደ ልጆች የተፈቀርን መሆናችንን ሊነግረን የሚችል እንዲሁም እኛ እግዚአብሔር እንደልጆቹ ለማፈቅርና በእርሱ የጸጋ ስጦታትና እርዳታ ደግሞ እንደእግዚአብሔር ልጆች ለመኖር እንችላለን፤ ልክ ኢየሱስ እንደ እግዚብሔር ልጅ ሆኖ እንደኖረው ለማለት” ሲሉ መንፈስ ቅዱስ የነፍሶቻችን ብርሃን መሆኑን አረጋግጠዋል፣
“መንፈስ ቅዱስ ምን ይለናል? እግዚአብሔር ያፈቅረሃል ይለናል! እኛስ ኢየሱስ አባቱን እንደወደደው ዓይነት እንደልጆቹ እግዚአብሔርን በእውነት እንወዳለንን? ጓደኞችንስ? መንፈስ ቅድስ ካልመራን ይህንን ለማድረግ አንችልም፣ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንዲመራንና በኅልናችን ድምጹን በመላክ እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ ሁሌ ይጠባበቀሃል፤ እርሱ እንደ እውነተኛ አባት ያፈቅረናል እውነትም ያፈቅረናል፣ መንፈስ ቅዱስም በኅልናችን ውስጥ ለልባችን የሚነግረን ይህንን ብቻ ነው፣ መንፈስ ቅዱስን እናዳምጥ እርሱን ሰምተን በዚሁ በፍቅር በርኅራኄና በምሕረት ጐዳና ወደፊት እንራመድ” ብለዋል፣
ቅዱስነታቸው የዛሬው ትምህርት መክፍቻ ያደረጉት በጸሎተ ሃይምኖት የምንደግመው ዓንቀጸ ሃይማኖት “ነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማሕየዊ፤ ጌታና ሕይወት ሰጪ በሆነው መንፈስ ቅዱስ አምናለሁ° የሚለውን በመጥቀስ ነበር፣ ይህንን መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠውን ሕይወት የሁሉ ዘመናት ሰዎች ፈልገውታል ይህንን ሕይወት መልካም ፍትሓዊና መልካም ሆኖ ከሞት ዛቻ ነጻ እንዲሆን ይፈልጋሉ፣
“የሰው ልጅ በምድረ በዳ እንደሚጓዝ የሃይማኖት መንፈሳዊ ንግደት እየፈጸመ ነው፤ በዚሁ ጉዞ ጥማት አለው፤ ይህንን ጥልቅ ጥማት የሚቆጭበትና በውስጡ ያለውን የብርሃን የፍቅር የበጎነትና የሰላም ፍላጎትም ለማርካት ንጹሕ ወራጅ ውኃ ለማግኘት ይሻል፤ ይህ ሰሜት ሁላችንን ያስጐመጅጃል!ኢየሱስም ይህንን ሕይወት ሰጭ ውኃ ይሰጠናል እርሱም ከእግዚአብሔር የሚሰርጽ እና ኢየሱስ በልቦቻችን የሚሞላው መንፈስ ቅዱስ ነው፣
ስለዚህ ለሰው ልጅ ሕይወት ውኃ መሠረታዊ እንደሆነ ሁሉ ለአንድ ክርስትያን እምነት መንፈስ ቅዱስ መሠረታዊ አስፈላጊነት አለው፤ ሕይወታችን በእግዚአብሔር እንድትመራ ሕይወት እንድታገንና በእርሱ እንድትመገብ ከሁለት ሺ ዓመታት በፊት ለሳምራዊትዋ ሴት ዛሬ ደግሞ ከሁለት ሺ ዓመታት በኋላ ለቤተ ክርስትያኑ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው የመንፈስ ቅዱስ ሕይወት ሰጪ ውኃ ተስፋ ገና ሕያው ነው፣
“መንፈስ ቅዱስ በልቦቻችን የሚያኖረው ክቡር ስጦታ ይህ ነው፣ የእግዚአብሔር ሕይወት የእውነተኞች ልጆች ሕይወት የመተማመን ግኑኝነት በእግዚአብሔር ፍቅርና ምሕረት ለመተማመን ነጻነት ማግኘት፤ በሩቅና ቅርብ ጓደኞቻችን ላይ ያለን አመለካከትም ሁላቸውን በኢየሱስ እንደወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ልናከብራቸውና ልናፈቅራቸው እንድሚገባን ሆኖ ይታደሳል፣ ሲሉ ካስተማሩ በኋላ በተለያዩ ቋንቋዎች አመስግነው ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.