2013-05-13 17:59:58

813 የኦትራንቶ ሰማዕታትና ሁለት የደቡብ አፍሪቃ ደናግሎች ቅዱሳን ተባሉ፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና በመንበረ ጴጥሮስ ባከናወኑት የቅድስና ሥርዓት የኦትራንቶ ሰማዕታትና እናቴ ላውራ ሞንቶያ እና እናቴ ማርያ ጓዳሉፐ ጋርስያ ዛቫላን ቅዱሳን ብለው በማወጅ በመንበረታቦት ካሳረግዋቸው በኋላ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል፣ እነኚሁ ቅዱሳን የፍቅርና የክርስትና ሕይወት ምስክርነት እንደሰጡም ገልጠዋል፣ ቅዱስነታቸው ስለዚሁ ምስክርነታቸው ሲገልጡ እንኚሁ ቅዱሳን ብሩህ የክርስቶስ ታማኝነት ምሳሌ መሆናቸውና በዚህም ምሳሌአቸው ክርስቶስ በቃላችንና በሕይወታችን እንድሰብከው ይህንን ደግሞ የእግዚአብሔርን ፍቅር በፍቅራችንና በመልካም አድራጎት እንድንመሰክር ይሁን እንደሚሉን ገለጠዋል፣
የእግዚአብሔር ቃል እስከ የሕይወት መሥዋዕትም ይሁን ታማኝነትን ይጠይቃል፣ ይህንን ታማኝነት ካሳዩት ዛሬ ቅዱሳን ብለን የምናውጃቸው 813 የሚሆኑ የኦትራንቶ ሰማዕታት ታላቅ ምሳሌ ናቸው፣ ጊዜው በ1480 ዓም ነበር፣ እነኚሁ ሰማዕታት ያኔ በኦቶማን ግዛት ሠራዊት ተከበው ለእምነታቸው ሲሉ ራሳቸው ተቆርጠዋል፣ ቅዱስነታቸው እነኚህ ሰማዕታት ይህን ያህል ኃይል ከየት አገኙት? ብለው ይጠይቃሉና እንዲህ ሲሉ ይመልሱታል፣
“በእምነታቸው ያገኙታል፤ ይህ እምነት ከሰው ልጅ አመለካከት ወዲያ በመሻገር ከምድራዊ ሕይወታችን ክልል በመሻገር እውነትን በማሳየት እንደ ቀዳሜ ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተከፈተ ሰማይን በማየት በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ያለውን ክርስቶስ በመመልከት ለማስተንተን ያስችላል፣ ውዶቼ መዝገባችን የሆነውን ከጌታ የተቀበልነውን እምነታችንን እንጠብቅ፤ በብዙ እንቅፋትና አለመረዳዳትና ችግር ብንገኝም በጌታ ያለንን እምነት እናሳድስ፣ እግዚአብሔር ደግሞ ታምኝ በመሆኑ በምንም ተአምር ኃይልና ሰላም ከመስጠታችን አይቆጠበም፣ የኦትራንቶ ሰማዕታትን ስናከብር ዛሬም ቢሆን በብዙ የዓለማችን ክፍሎች ብዙ ክርስትያኖች መሥዋዕት እየከፈሉ ስለሆነ እግዚአብሔር ጸጋውና ኃይሉን እንዲሰጣቸው እንለምነው፣ በተለያዩ ስደቶችና ስቃይ ለሚገኙ ክርስትያኖች የእምነት ብርታት እንዲሰጣቸውና እንደ ጌታም ለመጥፎ ነገር በመልካም ነገር እንዲመልሱ ያስችላቸው ዘንድ እንለምን” ሲሉ ባሁኑ ጊዜ ስለሚሰቃዩ ክርስትያኖች እንድጸልይ አሳስበዋል፣
ቅዱስነታቸው አያይዘው ስለሁለቱ ደናግሎች በማስተወስ ደግሞ በኮሎምብያ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስንና ወንጌሉን በታላቅ ደስታ ለማዳረስ ለስብከተ ወንጌል የተሰለፈችው እናቴ ላውራ ሞንቶያ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ነበር፣ መነኵሲትዋ መጀመርያ እንደ አስተማሪ ተል እኮዋን የጀመረች ሲሆን አያይዛም ለአገሩ ሰዎች መንፈሳዊ እናት በመሆን አገለገለች፣ የዚህች ቅድስት እናት መንፈሳዊ ልጆች ዛሬ በአገሩ ዋና የስብከተ ወንጌል ምንጭ ሆነው ይገኛሉ፣
“ይህች ቅድስት በኮሎምብያ የተወለደች ስትሆን ከእግዚአብሔር ጋር ለጋሶች እንድንሆንና እምነትን ለብቻችን ብቻ እንዳናደርገው ታስተምራለች፣ እምነትን በተናጠል ለብቻችን እንዴት መኖር ይቻላል ነገር ግን ለሌሎች ልናካፍለው ያስፈልጋል፤ የወንጌል ደስታን በቃልና በሕይወት ምስክርነት ለሌሎች ማዳረስ አለብን፣ ይህንን የምናደርገው ደግሞ በምንኖርበት አካባቢም ይሁን ዕድል ባገኝንበት በሁሉም ቦታ መሆን እንዳለበት ታስተምራለች፣ የኢየሱስ ገጽታ በሌሎች አንጸባርቆ እንደሚገኝ ለማየትና ለማወቅ ታስተምራለች፣ ይህ ድግሞ በዘመናችን ያለውን የግል ጥቅም ሱክቻና ግድየለሽነትን ለመሸንፍ ያስችለናል፣ ምክንያቱም ዛሬ ኅብረተሰባችንን በተለይ ደግሞ ማኅበረክርስትያንን እያማሰነ ያለው ሕመም በመሆኑ አለምንም ቅድመ ፍርድ አለምንም መለያየት ለሁላቸውን በእውነተኛ ፍቅር መቀበልና ማገልገል እንዳለብን ታስተማራለች፣ ይህንን የምናደርገው በተቻለን ያህል መልካሙን ነገር በማካፈል በተለይ ደግሞ ያለንን ታላቅ የእመንትና የፍቅር ስጦታ ክርስቶስና ወንጌሉ መሆን አለበት እንጂ በመዋቅሮቻችንና በተግባሮችን ይህንን እንዳንዘባርቀው መጠንቀቅ ያስፈልጋል፣
ቅዱስነታቸው ስለሌላው ቅድስት እናቴ ማርያ ጓዳሉፐ ጋርስያ ዛቫላ ሲናገሩ ምስክርነታችን ፍቅር የጐደለው እንደሆነ ፍሬ ለማስገኘት እንደማይቻል ሌላው ይቅርና ይህንን መልእልተ ባህርያዊ ኃይል ያልለበስን እንደሆነ ሰማዕትነትና ተል እኮ ክርስትያናዊ ጣዕማቸውን ሊያጠፉ እንደሚችሉ ገልጠዋል፣ ቅድስትዋ በ1878 ዓም በመክሲኮ ከሃብታም ቤተ ሰብ ተወልዳ ስለኢየሱስ ሃብቱንና ምቾቱን የመነነች ነበር፣ ይህንን ያደርገችው ደግሞ የኢየሱስ ጥሪን ለመቀበል ነበር በዚህም ሕመምተኞችንና ረዳት አልባ ለሆኑ ሰዎች ማገልገል ጀመረች፣
“ ይህ ማለትም የክርስቶስ ሥጋን መንካት ነው፣ ድሆች የተገለሉ ሕመምተኞችና ረዳት የሌላቸው የክርስቶስ ሥጋ ናቸው፣ እናቴ ሉፒታ ደግሞ የክርስቶስን ሥጋ ትነካ ነበር ይህንን ለማድረግ ማፈር እንደሌለብን የክርስቶስ ሥጋን መንካት ሊያስፈራን ወይንም ሊቀፈን እንደማይገባን ታስተምራለች፣ ይህች መክሲካዊት ቅድስት ኢየሱስ እንዳፈቀረን ሁሉ እኛም ማፍቀር እንዳለብን ታስተምረናለች፣ ይህን ለማድረግ ደግሞ ከገዛ ራሳችን ወጥተን ከገዛ ራሳችን ችግሮች አሳቦችና ጥቅሞች ወጣ በማለት እርዳታ የሚያስፈልጋቸው መረዳዳት የተነፈጋቸው ቅርበት የሚያስፈልጋቸው በክርስቶሳዊ ፍቅርና ጥንቃቄ በየዋህ ፍቅር ማገልገል ነው፣ ሲሉ ስለቅድስትዋ ልዩ ትምህርት ከገለጡ በኋላ ባጠቃላይ እነኚህ ቅዱሳን ዛሬ ለእኛ ምን እንደሚያስተምሩ እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“ለክርስቶስ ታማኝነቲ እንዴት ነው? ወደየቤታችን ስንመልስ ይህንን ጥያቄ በልባችን ይዘን እንሂድ፣ በቀረው የቀን ክፍለ ግዜ ለክርስቶስ ታማኝነቴ እንዴት ነው? እምነቴን ብክብር ለሌሎች ለማሳየት እችላለሁን? ይህንንስ በብርታት ነው ወይ የማደርገው? ስለሌሎችስ አስባለሁን! የተቸገሩ እንዳለሁ እመለከታለሁ ወይ? ለሁላቸው ወንድሞችና እኅቶች ፍቅር አሳያለሁን፧ ብለን ደጋግመን ራሳችንን እንጠይቅ፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም እና እነኚሁ አዳዲስ ቅዱሳን ጌታ ሕይወታችንን በፍቅሩ ደስታ እንዲሞላት ያማልዱልን ዘንድ እንማጠናቸው፣ ብለው ካሳሰቡ በኋላ ተፈሥሒ ኦ ንግሥተ ሰማይ ጸሎት አሳርገው ሐዋርያዊ ቡሪኬ በመስጠት ሕዝቡን አሰናብተዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.