2013-05-31 16:17:33

ጸረ ክርስቲያን አመጽ ነጋሪ የሌለው ዜና


RealAudioMP3 በየዓመቱ ከአንድ መቶ ሺሕ በላይ የሚገመቱ ክርስቲያኖች ከሃይማኖታቸውና ከእምነታቸው ጋር በተያያዘ የጥላቻ ምክንያት ለሞት እንደሚዳረጉ ባለፉት ቀናት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማዚ ባሰሙት ንግግር ክስ ማቅረባቸው ሲገለጥ፣ የተሰጠው መግለጫ በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ ስደትና መከራ እጅግ አስከፊና ያለፈ ታሪክ ሁነት ብቻ ሳይሆን ወቅታዊ መሆኑ የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስቲያን እንርዳ የተሰየመው የግብረ ሠናይ ማኅበር ቃል አቀባይ ማርታ ፐትሮሲሎ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ጸረ ክርስቲያ አመጽ ርእሰ ጉዳይ ሥር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ በማኅበረ ክርስቲያን ላይ የሚጣለው አደጋ እጅግ አሳሳቢ ሆኖ እያለ ነገር ግን የማይነገርለት ዜና፣ ወይም ነጋሪ ያጣ ዜና ሆኖ ይቀራል” ብለዋል።
የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስቲያን እንርዳ የተሰየመው የግብረ ሠናይ ማኅበር በአሁኑ ሰዓት በ131 ማኅበረ ክርስቲያን አብላጫ በሆነባቸው አገሮችና በ49 የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ብዙሃን በሆነባቸው በተለያየ መልኩ ጸረ ማኅበረ ክርስቲያን ድርጊት በሚፈጽምባቸው አገሮች በጠቅላላ በ 196 አገሮች ተሰማርቶ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፣ ከአርባ ዘጠኙ የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች አብላጫ ከሆነባቸው አገሮች ውስጥ በ11 የምስልምና ሃይማኖት አገራዊ ሃይማኖት ተብሎ በሕገ መንግሥት የተረጋገጠበት አገሮች መሆናቸው ገልጠዋል።
በእርግጥ ጸረ ክርስቲያን አመፅ ሰፊና አስጊ ሆኖ እያለ የክርስትና እምነት በሚገባ ካለ መኖር ምክንያት ይኽ ተጨባጭ አሳሳቢና አንገብጋቢ ጉዳይ የማይነገርልነት ዜና ሆኖ ይቀራል። በአሁኑ ወቅት እንደሚታየም፣ የክርስትናው እምነት ጥንታውያን ክርስቲያን አገሮች በሆኑም ሳይቀር የግል ጉዳይ ሆኖ እንዲኖር ይደረጋል፣ ሌላውን መቀበልና መለያውን ተክብሮለት እንዲኖር ለማድርግ የራስ መለያ ደብቆ ወይንም አፍኖ መኖር ከሚለው የተሳሳተ አመለካከት ጋር በማያያዝ ሲከወን ማየቱ ያሳዝናል፣ የራስ መለያ አለ ማክበር የሌላውን መጤ መለያ ለማክበር እንዴት ይቻላልን? ከዘመነ ዲዮክለዚያኑስ ጀምሮ ግብጽ በእምነት ሰማዕታት ደም የተነከረች አገር መሆንዋ አንድ የግብጽ ተወላጅ ካህን ያሉትን ቃል ፐትሮሲሎ አስታውሰው፣ የእምነት ሰማዕታት ደም ለአዲስ ክርስቲያን ዘር ነው የሚለው የተርቱሊያኑስ አባባል ጠቅሰው የምትሰቃየው ቤተ ክርስቲያን እምነት የምትመሰክር ቤተ ክርስቲያን ነች። እየተስፋፋ ያለው አክራሪነት ጸንፈኛነት የሚያባባሰው ስደትና መከራ፣ በመንግሥት ደረጃ የሚሰነዘር ሲሆን እጅግ አስከፊ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.