2013-08-02 15:21:51

ላምፐዱዛ፦ አንገብጋቢው የሕገ ወጥ ስደተኞች ጸአት


RealAudioMP3 የኤውሮጳ አገሮች የድንበር መቆጣጣር የጋራው ሥልት አስፈጻሚ ድርጅት ባለፈው ሳምንት ብቻ በባህር ጉዞ 1,300 የሕገ ወጥ ስደተኞች በኢጣሊያ ላምፐዱዛ ደሴት መግባታቸው በመጥቀስ በዚህ በቅርቡ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የጎበኘው ደሴት በኤውሮጳ ኅብረት አገሮች ማኅበር የሕግና ፍትኅ ሚኒስትሮችና የመከላከያ ኃይል ሚኒስትሮች ምክር ቤት ትላትና መጎብኘቱ ሲያመለክት፣ ስለ ስደተኞች ጸአትና በላምፐዱዛ ክልል ያለው የስደተኞች ሁኔታ በተመለከተ ጉዳይ በላፐዱዛ ቆሞስ አባ ስተፋኖ ናስታሲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ ጋር ባካሄዱት ቃል ምልልስ፦ በላምፐዱዛ ደሴት የስደተኞች ሁኔታ ሻል ያለ ቢመስልም ወደ ክልል በሚጎርፈው ስደተኛ ብዛት ጋር የሚስተካከል አዲስ የመርጃና ድጋፍ ማእከል አስፈላጊ ነው። የስደተኛው ቁጥር ብዛት እንዲህ ባለ መልኩ ከቀጠለ በርግጥ በስደተኞች ቁጥር ብዛት መጨናነቅ የሚታይበት የስደተኞች ጊዚያዊ የመጠለያ ሠፈር እጅግ ወደ ከፋና ወደ ተወሳሰበ ችግር እንዲያዘግም ሊያደርገው ይችላል ምክንያቱም የመጠለያ ሰፈሩ 400 ሰዎች ብቻ ለማስተናገድ ብቃት ያለው በመሆኑም ነው። የደሴቱቱ መስተዳዳር ነዋሪው ሕዝብ ለስደተኞች የሚሰጠው ትብብርና ድጋፍ የሚደነቅ ነው ነገር ግን የደሴቱቱ ትብብርና ድጋፍ ለብቻው በቂ አይደለም ብለዋል።
ላምፐዱዛ የተጋረጠባት ማኅበራዊ ችግር በቀላሉ የሚታይ አይደለም፣ መንግሥት ሌሎች የተለያዩ የመንግሥት ማኅበራት በደሴቲቱ ያለው የሰደተኞች ችግር ለማቃለል ቃል ይገባሉ እቅድ እንዳለም ያስታውቃሉ በርግጥ መልካም ፈቃድ ለብቻው በቂ አይደለም መልካሙ ፈቃድ በተግባር የሚሸኝ መሆን አለበት በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.