2014-06-27 17:47:18

እምነት የአጋጣሚ ጉዳይ ኣይደለም: ኢየሱስ የሕዝቡ ልብ ያሞቃል።


RealAudioMP3 ቅ.ኣ.ር.ሊ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ትናንትና በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ሕዝበ እግዚኣብሔር ኢየሱስን የሚከተለው እርሱ መልካም እረኛ መሆኑን ስለተገነዘበ ነው፣ ሲሉ ሃይማኖትን እንደማንኛው የግብረገብነት ትምህርት ኣድርገው የሚቀበሉና ለፖሎቲካዊ ነጻነት ለሚታገሉ ወይንም ከምድራዊ ስልጣን ጋር የለማጋራት የሚሞክሩ የተሳሳተ ኣስተሳሰብ መሆኑን ገልጠዋል፣
ቅዱስነታቸው የስበከታቸው መክፈቻ ኣድርገው የተጠቀሙት ጥያቄ “ኢየሱስን ለምንድር ነው ብዙ ሕዝብ ይከተለው የነበረ፦ የሚል ነበር፣ ሲመልሱትም በትምህርቱ ስለተማረኩና የጌታ ቃላት በልቦቻቸው ሙቀትና ኃይል እየሰጣቸው ኣንድ ደስ የሚል ታላቅ ነገር እንዳገኙ ሆኖ ይሰማቸው ስለነበር ነው፣ በኢየሱስ ዘመን የነበሩ ሌሎች ኣስተማሪዎች ብዙ ይናገሩ ነበር ነገር ግን የሰዎቹ ልብን ኣይነኩም ነበር፣
ኣያይዘውም በኢየሱስ ዘመን የነበሩ ሰዎች እንዴት ያሉና እነማን እንደነበሩ ለመግለጥ በኣራት ቡድን ከፋፍለዋቸዋል፣ ኣንደኛው ቡድን ፈሪሳውያን ሲሆኑ “የእግዚኣብሔር ኣምልኮ ያደርጉ ነበር እንዲሁም ሃይማኖትን ከእግዚኣብሔር ከፍ እንደማድረግ ዓይነት ያመልኩት ነበር በነበሩት ኣስር ትእዛዛት ሌሎች ስፍር ቁጥር የሌለባቸው ትእዛዞች በመዘርዘር ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ትእዛዞች ኣቁመው በምእመናኑ ላይ ይጭኑት ነበር፣ እንዲህ በማድረጋቸውም በሕያው እግዚኣብሔር የነበረውን እምነት እንደሌሎቹ የኣጋጣሚና የዕድል ነገር ኣደረጉት፣
“ለምሳሌ ያህል ኣንተ ኣራተኛውን ትእዛዝ መፈጸም ኣለብህ: ላረጀው ኣባትህና ላረጀችው እናትህ የሚበላና የሚጠጣ መስጠት ኣለብህ፣ ሲሉት ኣዎ እውነት ነው የሚገባም ነው ነገር ግን ገንዘቤን ሁሉ ለቤተ መቅደስ ስለሰጠሁ ምንም የለኝም ይላል፣ በዚህም እርሱ ለቤተ መቅደስ መባ ሲያቀርብ ሽማግሌዎቹ በረሃብ ይሞታሉ፣ ይህ ነው የኣጋጣሚ እምነት የሚያስከትለው ጭካኔና ተቃራኒ ሁኔታ፣ ሕዝቡ መማህራኑን ስለሚያከብራቸው ይታዘዝ ነበር ነገር ፈጽሞ ኣይሰማቸውም ነበር,”
ሁለተኛው ቡድን ደግሞ የሰዱቃውያኑ ነው፣ እነኚህ እምነት ኣልነበራቸውም፣ ኣጠፉት። የእምነት ቅጥረኝነታቸው በፖሎቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ ስልጣን እንዲራመዱ ኣደረጋቸው፣ የስልጣን ሰዎች ነበሩና፣
ሶስተኛው ቡድን በጊዜው ኣብዮታውያን ተብለው የሚጠሩ ቀናተኞች ነበሩ፣ የዚሁ ቡድን ኣባላት ሕዝበ እስራኤልን ከሮማዊ ግዛት ነፃ ለማውጣት ኣብዮት እናካሂድ የሚሉ ነበሩ፣ ሕዝቡ ግን ወዲያውያኑ ፍሬ ኣልባ መሆናቸውን ስለተገነዘበ ኣልተከተላቸውም፣
ኣራተኛው ቡድን በበጎ ሰዎች የቆመ የባህታውያኑ ቡድን ነበር፣ መነኩስየዎች ስለነበሩ ሕይወታቸውን ለእግዚኣብሔር የሰው ናቸው፣ ከሕዝቡ እጅግ ርቀው ይቀመጡ ስለነበርም ሕዝቡ ሊከተላቸው ኣልቻለም፣
ያኔ በሕዝቡ መካከል ይሰሙ የነበሩ ድምፆች እነኚህ ነበሩ፣ ነገር ግን ከእነዚህ ድምፆች ኣንድም የሕዝቡን ልብ ሊያሞቅ ሊያቀጣጥል የሚችል ኣልነበረም።
ኢየሱስ በደረሰ ጊዜ ግን ሕዝቡ በትምህርቱ ተማርከው ይሰሙትና ይከተሉት ጀምር እርሱ ሲናገር ልባቸው ይሞቅባቸው ነበር ምክንያቱም የኢየሱስ መልእክት በቀጥታ ልብን ይነካልና። ኢየሱስም በበኩሉ በሕዝቡ መካከል እየተመላለሰ ለሕዝቡ ቅርብ ነበር ልቦቻቸውን ይፈውስላቸው ነበር፣ ችግሮቻቸው ይረዳላቸው ነበር። የበለጠውኑ ደግሞ ኢየሱስ ከሓጢኣተኞች ጋር ለመናገር ምንም ኃፍረት ኣይሰማውም ነበር እንዲያው በየቤቶቻቸው ሄዶ ይጐበኛቸው ነበር፣ ከሕዝቡ ጋር ሲመላለስም ደስ ይለው ነበር ይህንን ያደርግበት የነበረበት ዋና ምክንያቱም እርሱ መልካም እረኛ ስለነበርና በጎቹም ድምጹን ደስ ብላቸው ሰምተው ይከተሉት ነበር።
“ለዚህም ነው ሕዝቡ ኢየሱስን ይከተለው የነበረው መልካሙ እረኛ ነውና፣ እላይ እንደተመለክትናቸው ፈሪሳውያን ሰዱቃውያን ቀናተኞች ወይም ባህታውያን ሳይሆን የሕዝቡ ቋንቋ የሚናገር የእግዚአብሔር ነገሮችን የሚነግር እና እውነትን የሚናገር ሆኖ ሕዝቡ ደግሞ በቀላሉ ይረዱት ነበር፣ ስለእግዚአብሔር ነገሮች ፈጽሞ ድርድር ውስጥ አይገባም ነበር እንዲያው ሕዝቡ የእግዚአብሔር ነገሮችን እስከሚያፈቅር ተወዳጅ በሆነ መንገድ ይነግራቸው ነበር፤ ሕዝቡም ለዚህ ይከተለው ነበር፣ ኢየሱስ ከአባቱም ይሁን ከሕዝቡ ከነጭራሹ ርቆ አያውቅም፣ ከአባቱ ጋር በነበረው ግኑኝነት ከአባቱ ጋር አንድ ነበር፤ እንዲሁም ለሕዝቡ ቅርብ ነበር፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሥልጣን ነበረው ለዚህም ሕዝቡ ይከተለው ነበር፣
“እስቲ ወደገዛራሳችን መለስ ብለን ለኔ ደስ የሚለኝ ማን ይሆን? ተጨባጭ ያልሆኑ ነገሮችና የግብረገብነት የአጋጣሚ ሁኔታዎች የሚናገሩ ወይስ የእግዚአብሔር ሕዝብ ነው ሲሉ በማታለል ካለው የፖሎቲካና ምጣኔሃብታዊ ሥልጣኖች ጋር የሚደራደሩ ወይንም ልዩ የሆኑ ነገሮች ለማድረግ ግርግር የነጻነት ውግያውችና የማይሆኑ ነገሮች የሚያደርጉ በመጨርሻ ግን የእግዚአብሔር መንገድ አለመሆናቸው ጎልቶ የሚያታዩ ነገሮችን የሚያደርጉ ወይንስ ከሁሉ ርቀው እንደባሕታውያን የአስተንትኖ ሕይወት የሚያሳልፉ? ማንን መከተል ደስ ይለኛል? ብለን እናስተንትን፣ ይህች ጥያቄ ወደ ጸሎት አድርሳ እግዚአብሔር አባታችንን ወደ ኢየሱስ እንድንቀርብ እርሱ ያለውን በመስማት ልባችን ተነክቶ እንድንከተለው ያድርገን ዘንድ እንለምነው ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ ዘወትር እንደሚያደርጉት ትዊተር በተሰኘው የዘመናችን መገናኛ ብዙኃን “የማንኛው የሰው ልጅና ማኅበራዊ ነዋሪ ሥልጣኔ መሠረት የሚሆነው ቤተሰብ ነው” ሲሉ በዚሁ አማካኝነት ለሚከታተልዋቸው ከአሥራ አራት ሚልዮን በላይ ለሚሆኑ ደንበኞቻቸው አጭር መል እክት እንድጻፉ ከቅድስት መንበር የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.