2014-08-06 18:50:11

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (06.08.14)


RealAudioMP3 ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ የበጋ ወቅት የዕረፍት ጊዜ ምክንያት ለሳምንታት አቋርጠውት የነበሩትን ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የሃገረ ስብከቱ ምእመናንና በተለያየ ምክንያት በሮም የሚገኙ ነጋድያን በተገኙበት “ጌታ ኢየሱስ ለሓዋርያቱ ያቀረበው የመጀመርያው ስብከት በመንፈስ ድኃዎች ብፁ ዓን ናቸው የሚለው ሲሆን ይህ መመርያ የኢየሱስ አጠቃልይ ትምህርትን የያዘ ሲሆን የእውነተኛ ደስታ መንገድም ነው” ሲሉ የብፅዓን ስብከት የአንድ ክርስትያን ሕይወት መስተዋት መሆናቸውን ገልጠዋል፣ ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስትያን የእግዚአብሔር ት እዛዛትን ብቻ ሳይሆን እነዚህንንም በቃል መያዝ እንዳለባቸው ካሳሰቡ በኋላ በአደባባዩ የተገኙት ሁላቸው ከእሳቸው በኋላ እንዲደግምዋቸው እንዳደረጉም ከቦታው የወጣ ዜና አመልክተዋል፣
ቅዱስነታቸው ያቀረቡት ትምህርት ከመላ ጐደል ይህንን ይመስላል፣ “ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! ባለፉት ትምህርቶቻችን ቤተ ክርስትያን እንዴት ኣንድ ሕዝብ እንደምታቆም: ሕዝቡም በእግዚአብሔር ትዕግሥትና ፍቅር እንደሚዘጋጅና እኛም የዚሁ ሕዝብ ኣባል እንድንሆን የተጠራን መሆናችንን ተመልክተን ነበር፣ ዛሬ ደግሞ ጌታ ኢየሱስ ሕይወቱን በመስጠት ያቆመው ኣዲስ ኪዳን የቆመውን ይህንን ሕዝብ ኣዲስ ሕዝብ ተብሎ እንዲጠራ ምክንያት የሆነውን ነገር ለመመልከት እወዳለሁ፣ ይህ ሕዳሴ በብሉይ ኪዳን የተደረገውን ጉዞ ኣይክድም ኣይቃውምም ነገር ግን ወደፊት እንዲራመድ በማድረግ ፍፅምና/ሙላት እንዲያገኝ ያደርገዋል፣
1. ብሉይ ኪዳንና ኣዲስ ኪዳን የሚያገናኝ ቁልፍ አለ! ይህም መጥምቁ ዮውሓንስ ነው፣ በ3ቱ ወንጌሎች እርሱ የጌታን መምጣት አስቀድሞ በመናገር ሕዝቡ ንስሐ እንዲገቡና ልባቸው የእግዚብሔርን መንግሥትና መጽናናትን እንዲቀበሉ የሚያዘጋጅ ጸያሔ ፍኖት ወይንም የጌታ ፊተውራሪ ነው። የዮሐንስ ወንጌል ክርስቶስን ሲመሰክርልን ኢየሱስ ከላይ ከሰማይ እንደሚመጣና ሐጢዓታችንን ሥርየት በማድረግ ሕዝቡን ለራሱ ሙሽራ ሊያደርግ ከሁሉም በላይ የመረጠው ሰውን ነው። መጥምቁ ዮሐንስ በመጀመሪያ የክርስቶስን መምጣት ያበሰረና የመሠከረ የመጽሓፍ ቅዱስ ዋና ቁልፍም ይህ ነው። እንደ ድልድይ በብሉይ ኪዳን
የነበሩትን ተስፋዎች እንዲፈጸሙ ሲገልፅ ከትንቢቶችም የተፈጸሙት የክርስቶስ መምጣትን ነው። ዩሐንስ መጥምቁ በምስክርነቱ ክርስቶስን ያሳውቀናል እንድንከተለውም ይጋብዘናል ያለ ምንም ጥርጥርም ትሕትና ንስሐና የልብ ለውጥ እንደሚያስፈልግ ይነግረናል።
እንደ ሙሴ ከእግዚብሔር ጋር የነበረውን ኪዳን 10ቱን ትዕዛዛት በሲናይ ተራራ በመቀበል እንዳከበረ ሁሉ እንዲሁም ኢየሱስ ከአንድ ተራራ በገለሊላ ወንዝ ኣጠገብ ለደቀመዝምርቱና ተሰብስቦ ለነበረው ሕዝብ አዲስ የቅድስና ትምህርትን አስተማረ። ሙሴ በሲናይ ላይ ትዕዛዞችን ሲቀበል አዲሱ ሙሴ የሆነው ኢየሱስ ደግሞ በገሊላ ወንዝ የብጽዕና ጐዳናን አስተማረ። የቅድስና ጐዳናው እግዚአብሔር የሚያመለክተው የሰው ልጅ በውስጡ ያለውን የደስታን ፍላጎት ለሟሟላት መልስ የሚሰጥ ነው። እነሱም የቀድሞውን የሕብረት ኪዳን የሆኑ ትዕዛዞቹን ካከበርን ነው። እኛ 10 ትዕዛዛት ለማክበር ተምረናል እርግጥ
ሁሏችሁም ታውቁታላችሁ በትምህርተ ክርስቶስ ተምራችሁታል ግን በቅድስና ለመኖር አልተለማመድንም! እስቲ ቅድስናን ለማስታወስ በልባችን እናትመው። አንድ ነገር እናድርግ እኔ ስላችሁ እናንተ ደግሞ ድገሙት ተስማማን! በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።
የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።
ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።
የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።
ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።

የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
እስቲ አንድ ነገር እናድርግ የቤት ስራ ልስጣችሁ፣ መጽሀፍ ቅዱስን አሁን በእጃችሁ የያዛችሁ ሁሉግዜ በቦርሳችሁም ይሁን በኪሳችሁ ትንሽዋን መጽሃፍ ቅዱስ እንድትይዙ አሳስባለሁ ዛሬ እውነተኛ ደስታ የሚለውን በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 5 ላይ ታገኙታላችሁ በድጋሜ አንብቡት ስለምታነቡትም አመሰግናለሁ። በነዚህ ቃላት ላይ ክርስቶስ የሰጠንን አዲስን ነገር ኣንደመለክታለን ይህም አዲስ ነገር ክርስቶስ እራሱ ነው። በእርግጥ ስለ ብፅዕና ስንመለከት ክርስቶስን ነው የሚገልጽልን የሱን ዓይነት ሕይወት መንገዱ ወደ ደስታ ሕይወት ያደርሳል እኛም ክርስቶስ በሚሰጠን ጸጋ ይህንን መንገድ መጓዝ እንችላለን።

2. ከአዲሱ ሕግ ባሻገር እየሱስ ሌላ እንዴት እንደምንፈረድ ይነግረናል። ዓለም ሲያልቅ እኛ ለፍርድ እንቀርባለን ምን ዓይነት ጥያቄ ይሆን እዛ የሚጠይቁን? ምን ዓይነት ይሆኑ እነዚህ ጥያቄዎች? የሚፈርደን ዳኛ በምን ስርዓት ይሆን የሚፈርደን? በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 25 በምናገኘው ነው። ዛሬ የቤት ስራችሁ የማቴዎስን ወንጌል ምዕ 5 እየሱስ በተራራው ላይ ያስተማረው ትምህርት እውነተኛ ደስታንና እንዲሁም ምዕ 25 በዓለም መጨረሻ በሚሆነው ፍርድ የምንጠየቀው በዛን ግዜ ንብረታችን ሃብታችን ዋስትና ሊሆኑን አይችሉም ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የሚያውቀን እኛም በተራችን ድሃውን የተጠማውንና የተራበውንና
የታመመውን በነሱ ክርስቶስን ካስተናገድን ብቻ ነው እዚህ ብቻ ናቸው ለኛ ለክርስትና ሕይወት መሠረታዊ በመሆን ክርስቶስ በየዕለታዊ ኑራችን እንድንኖር የሚፈልገው እውነተኛን ደስታን ሳነብ በየዕለቱ የክርስትና ሕይወቴ እንዴት መሆን እንዳለበት አስባለሁኝ እንዲሁም ማቴዎስን 25 በማንበብ የሕሊናን ምርመራ እናድርግ በየዕለቱ ይህንን ሰራሁ አደረግሁ ብለን ብናስብ ደስ ያሰኘናልን ቀላል ነገሮች ቢሆኑም ግን ተጨባጭ ናቸው።

ውዶቼ! አዲስ ኪዳንን የሚያቆሙ ዋና ነገር፣ በእግዚአብሔር ምሕረትና ርኅራኄ ተሸፍኖ ከክርስቶስ ጋር ኣንድ መሆን ነው፣ ልባችንን በደስታ የሚሞላው ደግሞ ይህ ነው፣ እንዲሁም ዘወትር በምናገኛቸው ወንድሞቻችን ፊት ላይ ሕይወታችንን በጎና ታማኝ የእግዚአብሔር ፍቅር ምስክር የሚያደርገው ይህ ነው፣ ሲሉ ካስተማሩ በኋላ በመጨረሻ የቤት ሥራችሁን ኣትርሱ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ኣምስትና ሃያ ኣምስት እንድታነቡት ይሁን! እግዚኣብሔር ይስጥልኝ በማለት ትምህርታቸውን ፈጽመው በተለያዩ ቋንቋዎች በማመስገንና ሓዋርያዊ ቡራኬ በመቸር ሕዝቡን ኣሰናብተዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.