2015-01-12 17:30:36

በፈረንሳይ ሁለት ሚልዮን ህዝብ አደባባይ ወጣ ፡


በፈረንሳይ ርእሰ ከተማ ፓሪስ ውስጥ ባለፉት ቀናት በሽብር ጥቃት የተገደሉ 17 ሰዎች ለማሰብ በ2 ሚልዮን የተሚገመት ህዝብ አደባባይ ወጥተዋል።
ሰልፉ የተካሄደው በጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቤተ ሰቦችን ጨምሮ ከዓለም ዙርያ የተሰባሰቡ የ60 ሀገራት መንግስታት መሪዎች ያከተተ ነበር ። በርካታ የተለያዩ ድርጅቶች የፖሊቲካ መሪዎች እንዲሁም የመገናኛ ብዙኀን ተቋማት ተወካዮች በዚሁ ውቅያኖሳዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተብሎ የተነገረለት ሰልፍ ተገኝተዋል።
ሰልፉ በከፍተኛ ተበቃ ታጅቦ መካሄዱ እና በፈረንሳይ ታሪክ እንዲህ ዓይነት ሰልፍ ሲካሄድ ይህ የትናትናው የመጀመርያ ግዜ እንደሆነም ተመልክተዋል።
ከ ሁለት 200 የሚበልጡ ጸጥታ አስከባሪዎች ከተማይቱን በየብስ እና በአየር ክልል ጸጥታ ማስከበራቸው ከፓሪስ ተገልጠዋል። በርካታ የእስላም እና አረብ ሀገራት መሪዎች በዚሁ የፓሪስ ሰላፍ ተሳታፊ መሆናቸው ታውቆዋል።
እንደሚታውሰው ባለፈው ሮቡዕ ዕለት ሻርሊ ኤብዶ በተባለ የምጸት መጽሔር መስርያ ቤት ውስጥ ሁለት ወንድማማቾች እንዲሁም አንድ ሌላ ሰው በአንድ የሸቀጥ መድብር ላይ ባደረሱት ጥቃት 17 ሰዎች መግደላቸው የሚታወስ ነው ። ከቀናት ክትትል በኃላም አሸባሪዎቹ በፖሊስ መገደላቸው የማይዘነጋ ነው ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ኢሲስ እና አል ቃዒዳ የተባሉ አሸባሪዎች አጋርነት ፈጥረው ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጁ መሆናቸው እየዛቱ መሆናቸው እየተነገረ ነው ።








All the contents on this site are copyrighted ©.