2016-03-10 17:22:00

ሴቶች በዓለም ዙሪያ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ወስጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።


በትላንትናው ዕለት ማለትም መጋቢት 8,2016 የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ በቫቲካን የሳይንስ መዕከል፣ ሴቶች በዓለም ዙሪያ ሁሉ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ወስጥ  ሰለ ሚጫወቱት ሚና ትኩረት ሰጥቶ መነጋገሩን እና ይህም ጉባሄ በፊደል ጎዝ ማህበር እና በኢየሱሳዊያን የስደተኞች ማህበር ትብብር መዘጋጀቱ ታወቀ።

ይህ ትላንትና ከስዓት ቡኋል የተካሄደ ውይይት ብዙ ተጋብዥ እንግዶችን ያሳተፈ እና የስብሰባው እርዕስ እንዲሆን የተመረጠውም “ምህረት ድፍረትን ይጠይቃል” የሚልው ስሆን ይህም አርዕስት የተመረጠው ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮስ ባወጁት ልዩ ቅዱስ የምህረት ዓመት ጋር እንዲስማማ ተደርጎ መሆኑ በስብሰባው ወቅት ተውስቶ፣ የተመረጠው አርዕስት በተጨባጭ የእግዚኣብሔርን የምህረት በረከት የቀመሱ የሴት እና ወንድ የስብሰባ ተካፋይ ሰዎችን ሕይወትም የሚዳስስ በመሆኑ ምርጥ ሊባል የሚገባው አርዕስት እንደ ሆነ በውይይቱ ወቅት የተገኙ ኢየሱሳዊያን የስደተኞች ማህበር ሀላፊ አባ ቶማስ ስሞልኪ ገልጸዋል።

ሴቶች ከወንዶች አንጻር በቤትክርስቲያናችን ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር እንደ ሚሸፍኑ የሚታወቅ ስሆን ለቤተክርስቲያናችንም የሚያበረክቱት አገልግሎት ከፍተኛ በመሆኑ ልመሰገኑ እንደሚገባ በጉባሄው ወቅት ተገልጾ፣ የስብሰባውም ዋና ዓላማ ይህንን ሴቶች እያበረከቱ የሚገኝወን አገልግሎት እውቅና በመስጠት ለማመስገን ስሆን በተጨማሪም የተለያየ ማህበረሰባዊ ጫና የሚደርገባቸው ሴቶችን ለማስታወስ እና ከዚህ ባህበራዊ የጭቆና ቀንበር ሥር ለመውጣት በድፍረት ይታገሉ ዘንድም ለማሳሰብ መሆንም ታውቁኋል።

በዓለም ዙሪያ የተደርገ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ 85 በመቶ የሆነው (ለሚስጢረ ክህነት አገልግሎት ከተሰጠ ተግባር ውጭ) የሆነው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚሸፈነው በሴቶች መሆኑ በጥናት የተደረሰበት ስሆን በተለይም በአሜርካ ማህበረሰብ ውስጥ በማህበርሰቡ እና በቤተክርስቲያን ወስጥ የሴቶች ሚና እጅግ በጣም ክፍተኛ መሆኑን ከውይይቱ ለመረዳት ተችልኋል።

ዓልም አቀፍ የሴቶች ቀን በየዓመቱ የሚከበር ስሆን የተጀመረውም እንደ አውሮፓዊያን የዘመን አቆጣጠር 1909 በአሜርካ ስሆን በ1945 በተባበሩት መንግሥታት ድርጅ ሴት እና ወንድ በማንኛወም የማህበርሰብ ክፍል ወስጥ የእኩልነት ሚና እንዲኖራቸው ከተወሰነ ቡኋላም በተለያዩ የዓልም ክፍሎች ቀኑ እየተከበር በአሁኑ ወቅት በዓለማቀፍ ደረጃ 105ኛ ጊዜ በኢትዮጲያ ደግሞ ለ40ኛ ጊዜ መከበሩ አይዘነጋም።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.