2016-04-04 16:29:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ብፁዕ ጳውሎስ ስድስተኛ እውነተኛ የወንጌል አገልጋይ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ የፊረንዘው የአረጋውያን መጠጊያ ማእከል ጳውልስ ስድስተኛ ዝርከ 45ኛው ዓመተ ምሥረታ ምክንያት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ፊርማ የተኖረበት ለፊረንዘ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጁዘፐ በቶሪ ባስተላለፉት መልእክት፥ ማእከሉ እ.ኤ.አ. ህዳር 4 ቀን 1966 ዓ.ም. በፊረንዜና አካባቢ ተከስቶ በነበረው ኃይለኛ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ መጥለቅለቀ አደጋ ሳቢያ ለተጎዱት ሁሉ እርዳታ በማቅረብ በተለይ አለ ቤትና ንብረት የቀሩትን ሁሉ ለማስተናገድ በሚል ዓላማ በር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ጳውሎስ ስድስተኛ መመስረቱንም አስታውሰው፥ ማእከሉ ብፁዕ ጳውሎስ ስድስተኛ ለሕዝብ ቅርብ መሆናቸውና ባለንጀራህን እንደ ገዛ እራስ አፍቅር የሚለው የጌታ ጥሪ የሚመሰክር ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የማእከሉ ዝክረ 45ኛው ዓመት ምሥረታ ምክንያት በፊረንዘ ካቴድራል በብፅዕ ካርዲናል በቶሪ ታጅበው የከተማይቱ የመንግስት ተጠሪዎችና የመስተዳድር ምክር ቤት አባላትና ምእመናን ያሳተፈ መሥዋዕተ ቅዳሴን የመሩት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ብፅዕ ጳውሎስ ስድስተኛ ያሠሩት የአዛውንት ማእከል ቤተ ክርስቲያን ለሚጎዳው ቅርብ መሆንዋ የሚመሰክር የፍቅር ሥራ ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎ ያመለክታል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም የፊረንዘ ሰበካ ባከበረው የፊዮረንቲና ተወላጅ ቅድስት ማሪያ ማዳለና ዘፓዚ የቀርመሎሳውያን ደናግል ማሕበር አባል በ 16ኛው ክፍለ ዘመን በሕይወት የነበረቸው በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ር.ሊ.ጳ. ክለመንተ ቅድስና ላወጁላት ዝክረ 450ኛው ዓመተ ልደት ምክንያት ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓርሊኒ መርተው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የዋና ጸሓፊው ፊርማ የተኖረበት ያስተላለፉት መልእክት ለፊረንዘ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል በቶሪ ማስረከባቸውና ብፁዕ ካርዲናል በቶሪ መልእክቱን ለምእመናን ያነበቡም ሲሆን። ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት ቅድስት ማሪያ ማዳለና ዘፓዚ ፍቅርን በመኖር ለጌታ ያላት ፍቅር ድኾችን በማገልገል ብቻ ሳይሆን እነርሱን በመምሰል ወደ ክርስቶስ መምሰል ያደገች ነች እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.