2016-11-05 11:01:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በጥቅምት 24/2009 ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት የተውጣጡ ተወካዮች ጋር በቫቲካን ተገናኙ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 24/2009 ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ለተውጣጡ ተወካዮችን በቫቲካን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት የሁሉም የሐይማኖት ተቋማትና የተለያዩ ሐይማኖት ተከታዮች ሰላማዊ የሆነ ግንኙነት እንዲኖራቸውና እውነተኛ የሆነ የሐይማኖት ነፃነት እንዲኖር መጣር እንዳለባቸው መግለጻቸው ተዘገበ።

ከ200 በላይ የሚሆኑና የተለያየ ሐይማኖት ተወካዮች በቫቲካን የተዘጋጀውን የውይይት ስብሰባን ለመታደም በተገኙበት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ አድርገውት የነበረው ንግግር የጀመረው ከባለፈው ዓመት ማለትም ከኅዳር 29/2008 ዓ.ም ጀምሮ ለ349 ቀናት ያህል ልዩ ልዩ መንፈሳዊና አካላዊ የምሕረት ተግባራት እየተከናወነ የሚገኘው ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመት በቅርቡ ማለትም ከ17 ቀናት ቡኋላ በኅዳር 11/2009 ዓ.ም የሚጠናቀቅ መሆኑን በማውሳት ንግግራቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው “ቅጥ ያጣና በስግብግብነት እየተፈጸመ ከሚገኘው ፍጆታ የጋራ መኖሪያችን እንድንከላከላት ለተጠራንበት” በዙሪያችን ያለው ዓለም ምሕረት ዘልቆ ሊገባ እንደ ሚገባ ገልጸኋል።

በዛሬ ወከባ በበዛበት እና በተረሳችው ዓለማችን እኛ የለምንም ቅድመ ሁኔታ ሕይወት ሰጪ የሆነው ኦክሲጂን ያስፈልገናል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ምሕረትን ተጠምተናል የተኛውም አይነት ተክኖሎጂ ይህንን ጥማታችን ልያረካ አይችልም” ካሉ ቡኋላ “ከጊዜያዊ ደስታ ባሻገር ያለውን ዘላቂ ፍቅርና አስተማማኝ የሆነ፣ ረፍት የለሽ መቅበዝበዛችን ማብቂያ የሚያገኝበት፣ በይቅርታና በእርቅ የሚተቃቀፍ መኖሪያ ነው የሚያስፈልገን” ብለኋል።

ቅዱስነታቸው በተጨማሪም ለስብሰባው ተሳታፊዎች እንደገለጹት “ግብረገባዊ የሆነ ትምሕርት እንዲኖር፣ መከባበር እንዲሰፍን፣ ይበልጥ ቀላል የሆነ ሕይወት ይኖር ዘንድና ሕይወት ሥርዓት ባለው መንገድ እንዲቀጥል” ለማድረግ የጋራ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል ብለዋል።

ከሁሉም በላይ የሁሉም የሐይማኖት ተቋማት አለመግባባትን የሚፈጥረውን ጥላቻና ትምክተኛነትን አስወግደው የውይይት ባሕልን ማዳበር እንደ ሚጠበቅባቸው በመገልጽ ንግግራቸው የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የአንድ አንድ ሐይማኖት ተከታይ ምዕመናን ከምሕረት ተግባራት ቅኝት ውጭ ሆነው በምያስተላልፉት እኩይ በሆነ ምልዕክት  ላይ ተመርኩዘን ልዩነቶች እንዲፈጠሩ በፍጹም መፍቀድ የለብንም ብለዋል።

“በሚያሳዝን ሁኔታ በእየለቱ የጥቃት ድርጊቶች፣ ጦርነቶች፣ አፈና፣ የሽብር ጥቃቶች፣ ግድያ እና ውድመት ሳንሰማ ያለፍንበት ቀን የለም” ያሉት ቅዱስነታቸው “አንዳንድ ጊዜ ይህ አሰቃቂ የጭካኔ ተግባር የሚፈጸመው በሐይማኖትና በእግዚኣብሔር ሥም ሲፈጸም ማየት በጣም ያሳዝናል” ብለዋል። እነዚህን የእግዚኣብሔርን ሥም የሚያጎድፉና የሰው ዘር ሁሉ ያለውን  የሃይማኖት ጥማትን የሚያጎድፉ ተግባራትን በግልጽ ማውገዝ ይጠበቅብናል ብለዋል።

የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን በመቀጠል ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ለተውጣጡ ከ200 በላይ ተወካዮች ያደረጉትን ንግግር እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ጉዋደኞቼ!

ሞቅ ያለ ሰላማታን አቀርብላችኋለሁ። ምሕረት በሚለው ጭብጥ ላይ የተዘጋጀውን አስተንትኖ እንድትካፈሉ ያቀረብኩላችሁን ጥሪ ተቀብላችሁ እዚህ በመገኘታችሁ ደስታዬን እየገለጽኩኝ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

እንደ ሚታወቀው በያዝነው ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የምሕረት አመለካከቷን የክርስቲያኖቿ ልብ ውስጥ ተጠብቆ ይኖር ዘንድ ለማስቻል በማሰብ የተዘጋጀው የምሕረት ዓመት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል። ለእኛ ምሕረት የእግዚኣብሔር ስም መገለጫ ነው፣ “የቤተ ክርስቲያናችንም ሕይወት ሥር መሠረት ነው” (Misericordiae Vultus, 10)። እንደዚሁም ደግሞ የሰው ልጅ ምሥጢራዊነትን ለማስረዳት ቁልፍ የሆነና ዛሬም ቢሆን ምሕረትና ሰላም እጅግ አስፈላጊ በሆነበት ወቅት የሰው ልጅ ስብዕናን መግለጫም ጭምር ነው።

የምሕረት ምስጢራዊነት በቃል ብቻ የሚገለጽና የሚከበር ሳይሆን ነገር ግን ከሁሉም በላይ በተግባር፣ እውነተኛ በሆነ በፍቅር፣ ወንድማቻችንን በማገልገልና ቅን በመሆነ መልኩ ያለንን ማጋራት የሚገለጽ ነው። በተክርስቲያናችን ይህንን ዓይነት የሕይወት መንግድ ለመከተ በከፍተኛ ሁኔታ ትሻለች፣ እንዲሁም ግማሽ አካሉዋ በሁሉም ሰዎች መካከል “አንድነት እና ፍቅር እንዲሰፍን የማድረግ ተግባር” ተስቱኋታል (Nostra Aetate, 1)። በተመሳሳይ ሁሉም ሃይማኖቶች ይህንን የሕይወት መንገድ እንዲከተሉ የተጠሩ ሲሆን በተለይም አሁን ባለንበት ወቅት የሰላም መልዕክተኞችና መልካም ግንኙነቶችን የሚያቀላጥፉ፣ ጥላቻን፣ መከፋፈልንና አለመቻቻልን የሚዘሩትን እንዲያወግዙ፣ እኛ ያለንበት ወቅት የወንድማማችነት እንደ ሆነ እንዲመሰክር ነው የተጠራነው። ተገናኝተን የመነጋገራችን ሐላማ ይህ ነው፣ ይህም ግንኙነት ላይ ላዩን የሚታየውን የሐይማኖት ሕብረትን በማስወገድ “ለውይይት ዝግኙ በመሆን እርስ በእርሳችን በተቻለ መጠን ለመተዋወቅና የጥላቻ እና የመከፋፈል ምንጭ የሆኑትን እርስ በእርሳችን ያለመተዋወቅ፣ የጠባብነት፣ የትምክተኝነትና ያለመከባበር ዝንባሌን ማስወግደ ይጠበቅብናል (Misericordiae Vultus, 23)። ይህም ተግባር እግዚኣብሔርን የሚያስደስትና በፍጥነትም ለአሁኑ ጊዜ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ከሁሉም በለይ የሁሉም ሐይማኖት መጠርያ ወይም መለያ የሆነውን ፍቅርን ማረጋግጥ ያስችለናል።

የምሕረት ጽንሰ ሐሳብ ርኅራኄ እና ኃይልን አለመጠቀም አስፈላጊ የሕይወት ንጥረ ንግሮች ናቸው በሚሉ ሐይማኖትና ባህላዊ ወጎች ሁሉ ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ የሚገለጽ ሲሆን በአንድ ጥንታዊ ምሳሌ እንደ ተገለጸው “ሞት ከባድና የሚያዝል ወይም አድካሚ ነገር ነው፣ ሕይወት ግን ቀላልና የተሟላ ነው” (Tao-Te-Ching, 76)። ርኅራኄ በተሞላው ፍቅር በደካማና በተቸገረ ሰው ፊት መንበርከክ ጉልበትን መጠቀም አድናወግዝ፣ የሰውን ሕይወት በገንዘብ ከመለወጥ በመቆጠብ ሰዎችን ሁሉ እንደ ወንድም እና እህት እንድንመለከት እንዲሁም በስሌት ላይ የተመሰረተ እርማጃን የምያስወግድ የሐይማኖት እውነተኛ መንፈስ ነው። አሳሳቢ ሁኔታዎች ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ለምሳሌም፣ የታመሙትን፣ አካለ ጉዳተኛ የሆኑትን፣ ድኾችን፣ ፍትህ ያጡትንና ከሁሉም በላይ ደግሞ የጦርነት ሰለባ የሆኑትንና ስደተኞችን በደንብ በመቅረብ የሁሉም ትክክለኛ ሐይማኖቶች መገለጫ ባህሪ ነው። ይህም በሁሉም መንፈሳዊ ሰዎች አዕምሮ ውስጥ የሚያቃጭል መንፈሳዊ ድምጽ በመሆኑ ራስ ወዳድነትን በማስወገድ ለሁሉም ልባችንን ክፍት እንድናደርግ የሚያሳስበን ጥሪ ነው። ከጎናችን ሆነው የልባችንን በር ለሚያንኳኩ በሌላ በኩል ደግሞ የኛን ትኩረትና እርዳታ ፈልገው የቤቶቻችንን በር ለሚያንኳኩ ሰዎች በራችንን ክፍት ማድረግ ያስፈልጋል።

“ምሕረት” የሚለው ቃል  የተከፈተና የሚራራ ልብን ይገልጻል። ይህም ቃል በላቲን ቋንቋ ላይ መሰረቱን ያደረገ ሲሆን misericordia ከሚለው ቃል ውስጥ cor የሚለው ለማንኛውም ስቃይ የሚሳሳ ልብን የሚያመለክትና በተለይም ደግሞ በጣም የሚሰቃዩ ሰዎችን የተመለከተና ልዩነቶችን አስወግዶ የሌሎችን ስቃይ የሚጋራ ልብ ማለት ነው። በሴማዊ ቋንቋዎች ለምሳሌም በአረብኛና በህብራይስጥ RHM ከየሚለው ሐረግ የሚያመለክተው የእግዚኣብሔርን ምሕረት የሚገልጽ ሲሆን ይህም በቀጥታ የሰው ልጆች የፍቅር ምንጭ የሆነውን የእናት ማህጸንንና እናት ለምትውልዳቸው ልጆቿ የምታሳየውን ፍቅር የሚገልጽ ሐረግ ነው።

በእዚህም ረገድ ነቢዩ ኢሳያስ በእግዚኣብሔር በተመለከተ  በጣም የጎላ መልዕክት በማስተላለፍ የሚያቀርብልን የፍቅር ቃል ኪዳንና ተግዳሮቶቹን በመግለጽ “እናት የምታጠባውን ልጅ ልትረሳ ትችላለችን? ለወለደችሁ ልጅ አትራራምን?ምናልባት እርሷ ልጆቹኋን ትረሳ ይሆናል እኔ ግን በፍጹም አልረሳቹም” (ኢሳያስ 49.15)። የሚያሳዝነው ነገር ብዙን ጊዜ ልባችን ዘንጊና እና ግድ የለሽ ሆኖ እያደገ መሆኑን እንረሳለን። ራሳችንን ከእግዚኣብሔር፣ ከጎሬቤቶቻችን እንዲሁም ታሪካዊ የሆኑ ትውስታዎችን ለምሳሌም ያለፉትን ጨካኝና አስፈሪ ስተቶቻችንን ራሳችንን እናርቃለን።

ዛሬ ባልንበት ወቅት በሰፊው የሚንጸባረቀውን “ይቅር ልባል አልችልም” የሚለው ፍራቻ በተሃድሶ ከድክመታችን መላቀቅ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው። ለእኛ ለካቶሊኮች በእዚህ ልዩ ቅዱስ የምሕረት አመታችን ትርጉም የሚያሰጠው ስርዓት በትህትናና በቅዱስ በሩ በመታመን የምናደርገው ንግደት በእግዚኣብሔር ምሕረት መጎብኘታችንና ከእርሱ ጋር መታረቃችንን የሚያሳይና መተላለፋችን የሚደመሰስበት ወቅት ነው። ነገር ግን ይህ ተግባር ተፈጻሚነትን የሚያገኘው “እኛን የበደሉንን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ይቅር ማለት ስንችል ብቻ ነው (ማቴዎስ 6.12)። የእግዚኣብሔርን ምሕረት የምንቀበለው ከሌሎች ጋር ይህንን ምሕረት ለመካፈል ነው።

ለሰዎች የምንሰጠው ትልቁ ስጦታ ይቅርታን ማድረግ ነው ምክንያቱም በጣም ውድ የሆነ ስጦታ ስለሆነና በተመሳሳይ መኩም እግዚኣብሔርን እንድንመስል ስለ ምያደርገንም ጭምር ነው።

ይህም የምንራመድበት ጎዳን ይሁን። ዓላማ የለሽ የሆነውን የአለመግባባት መንገድና ትምክተኛነትን እናስወግድ። በአንድ አንድ አማኞች ምክንያት በሚፈጸመው ጥቃት ምክንያት የሚሰራጨው አፍራሽ መልዕክት ከምሕረት ተግባራት ቅኝት ጋር የማይመጣጠን በመሆኑ በድጋሚ እንዳይከሰት መጣር ያስፈልጋል። በአንጻሩም በሁሉም ስፍራዎች የተለያየ ሐይማኖት ተከታዮች ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲገናኙና እውነተኛ የሐይማኖት ነጻነት እንዲመጣ መጣር ያስፈልጋል። ይህም በእግዚኣብሔር ፊት፣ በሰዎችና በመጭው ጊዜ ላይ የተሰጠን ኋላፊነት ነው፣ ይህም የማያባራ ጥረት የሚጠይቅ እና ያለ ግብዝነት መፈጸም ይኖርበታል። ለሁሉም መልካምነት በተስፋ አብሮ የሚያስጉዘንን ጎዳና እንድንይዝ  የቀረበ ጥሪ እኛ የሚፈታተን ጥሪ ነው።

ሃይማኖቶች በችግሮች የቆሰለውንና ችግረኛ ለሆኑ የሰው ልጆች የእግዚአብሔር ምሕረትና ፍቅር የሚሸከመውን  ሕይወት የሚያመነጭ መሃጸን እንዲሆኑ፣ ኩራት እና ፍርሃት ባጸኑት ግድግዳዎች ውስጥ ዘልቆ የመርዳዳትን የተስፋ በሮች እንዲከፈቱ ማድረግ ይገባል በማለት ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.