2016-12-29 11:26:00

ከቫቲካም ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የእለተ ርዕቡ የታኅሣሥ 19/2009 ዓ.ም. ዜና።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በታኅሣሥ 19/2009 ዓ.ም. በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተገኙበት ያስተላለፉት የጠቅላላ አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው የክርስቲያን ተስፋ በሚል ጭብጥ ዙሪያ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አደራችሁ! ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ አብርሃም የነበረውን ታላቅ ገጽታን በማስታወስ የእምነትን እና የተስፋን መንገድ ያሳየናል በማለት አስተምህሮዋቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው ስለ አብርሃም ጳውሎስ “አብርሃም ያመነው እና ተስፋ ያደረገው ምንም ተስፋ ባልነበረበት ጊዜ ነው፣ ስለዚህም የብዙ ሰዎች አባት ሆነ” (ሮሜ 4,18) ብሎ እንደ ጻፈ አስታውሰው ምንም ተስፋ ባልነበረበት ወቅት ተስፋ ማድረግ መቻሉ በራሱ በጣም ከባድ ነገር ነው ካሉ ቡኋላ አብርሃም ይህንን ተስፋ ያገኘው እግዚኣብሔር ያለውን ነገር ሁሉ በእምነት አምኖ መቀበል በመቻሉ እና ሚስቱ መሃን በመሆኑዋ የተነሳ እና እርሱም በእድሜ የገፋ ሰው በመሆኑ ምክንያት የቆረጠውን ተስፋ መልሶ ማለምለም ችሎ ነበር ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.